ላለፉት 25 ኣመታት የሰለጠኑ ሳይሆን የተሰደዱ ዜጎችን ያፈራ የወያኔ ኣገዛዝ ፈተና ውስጥ ነኝ አያለ ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኣንድ ኣገር ኣገዛዝ ትክክለኛ ኣስተዳደር የሚተገብር ከሆነ አጅግ የበለጸገ አና የሰለጠነ ትውልድ ያፈራል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ኣይሰራም። ባለፉት 25 ኣመታቶች ስልጣኑን ኣንቆ ኣለቅ ያለው ወያኔ የሰለጠኑ ዜጎችን ከማፍራት ይልቅ የሚሰደዱ ዜጎችን በማፍራት በኣለም ኣቀፍ ደረጃ ከጦርነት አና ከችግር ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ከገቡ ኣገሮች በላይ የመጀመሪያ ረድፍ ላይ ይገኛል። በሃገሪቱ ባለፉት ኣመታቶች ሰልጥነዋል ስልጣን በስልጣን ላይ ተደራርቦላቸዋል በሃገር አና ሕዝብ ሃብት በልጽገዋል ሰው ሃገር ድረስ ሄደው ተምረዋል የሚባሉት አጅግ ጥቂቶች ሁለት በመቶ የማይሞሉ በጎሳ መንደር የተፈለፈሉ በመንደርተኝነት የተሰገሰጉ “ኣናሶች” ናቸው።
ብዙሃኑን ከማሰልጠን ይልቅ ማሳደድ ላይ ያተኮረው ኣገዛዝ ዛሬ ላይ ተቀምጦ መጣፊያው ቢያጥረው በሰራው ስሕተት ሳይጸጸት ካለፈው መማር የማይሆንለት የወያኔ ጉጅሌ ኣገዛዝ በሰለጠነ የሰው ሃይል ችግር ፈተና ውስጥ ነኝ ሲል አያማረረ ይገኛል።በሃገሪቱ ሊሰራ የሚችለው ወጣት የተማረ ሃይል ይሁን ያልተማረው ከሃገሪቱ ተሰዶ በተለያየ መስክ የልጥሎች ሃገራትን ኢኮኖሚ አያዳበረ ይገኛል፤በፖለቲካ ጫና በኢኮኖሚ ጠረባ በማህበራዊ ችግር ኣገዛዙ በፈጠረው አንቅፋት የመኖር ሕልውና በማጣቱ በኣሁኑ ወቅት የሚፈለገው የሰው ህያል በየሰዉ ኣገር ኣገሩ የተነሳውን ስራ ኣንገቱን ደፍቶ አየሰራ ይገኛል።ይህ አንዲሰደድ የተደረገው የሰው ሃይል አንዲሰደድ መንገድ ባይመቻችለት ኖሮ ኣገሪትዋ የምትፈልገውን የልጆችዋን ድጋፍ ኣታጣም ነበር፥ሆኖም የስርዓቱ ጋጥ ወጥነት ዜጎች በሃገራቸው ሰርተው አንዳይበሉ ጫና ስለፈጠረ ተሰደዋል ኣገዛዙም ከባድ ፈተና ላይ ወድቋል ይህ መንደርደሪያ ውድቀት ነው::
የግብርናውን መስክ በስርዓት መምራት ያልቻለ ኣገዛዝ ለወገን የተፈጥሮ ኣደጋ በቂ ዝግጅት አና ለኣደጋ መድረስ ያልቻለ ኣገዛ በምግብ አህል ራሱን ያልቻለ የግብርና የሚተዳደህ ሕዝብ በሞላበት ኣገር ኢንዱስትራላይዝshን ብሎ መነሳት በሕዝብ ላይ ከማሾፍ ኣይተናነስም፥በሃሰት ኣገር አየመሩ በማጭበርበር የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ላይ የተመሰረቱ ባለስልጣኖች ከባዱን የሃገር መሰረት በማናጋት ሊወጡት የማይችሉት የኢኮኖሚ መፍረስ ቢገጥማቸውም የነፍስ ወከፍ ገቢ 1200 ዶላር አናደርሳለን በማለት አየተቀደዱ ይገኛሉ፥፥ሆን ተብሎ ባልተጠና ፖሊሲ ገበሬውን የከተማ ጥገኛ ለማድረግ ቤተሰቡን ለመበተን መሬት ኣልባ ኣድርጎ የጎዳና ተዳዳሪ ለማድረግ የሚደረግ ሩጫ ክላሆአ በስተቀል ላለፉት ሃያ ኣምስት ኣመታት ያየናቸው የእድገት አና ትራንስፎርሜኅን አቅዶች ምንም ያልተሳኩ ራእይ ኣልባ አንደነበሩ ከኽፈታቸው ኣይተናል። በየኣመቱ መዋቅራዊ ለውጥ የሚያደርገው የወያኔ ኣገዛዝ ኣሁንም መዋቅራዊ ለውጥ በማድረግ አንደገና ወደ ባሰ የድህነት ኣዘቅት ህዝብን ለመክተት ታጥቆ ተነስቷል፤የወያኔ ኣገዛዝ በጊዜ ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ ሲገባው ባልተጠናና አንጭጭ በሆነ ፖሊሲው ሕዝብን ለድህነት ሃገርን ለውድቀት አየዳረገ ስለሆነ ጥንክረን ልንዋጋው ይገባል፥ኢትዮጵያ ውስጥ የጉልቻ አና የመዋቅር ለውጥ ሳይሆን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል። #ምንሊክሳልሳዊ
