ብልግናና እና ስልጣን ( ሄኖክ የሺጥላ )


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ብልግናና እና ስልጣን ( ሄኖክ የሺጥላ )

ባለጌ ብልግናውን በትምህርት ፣ በሥርዓት በተገመደ ባህል ፣ በቤተሰብ እና በሚከተለው ሃይማኖት ካላረቀ ዱርዬ ይሆናል ። ይህ ዱርዬ ወታደር ከሆነ ደሞ ፣ የጠመንጃው አፈሙዝ እና ብልግናው ጥጋብ ይደርብለት’ና የወጣለት አምባገነን ይሆናል ። የኢትዮጵያ ችግር ይሄ ነው ። አመጸኛ ባለጌ ጀግና ሆኖ ፣ የሚፈራው አጣ ፣ የሚያከብረው አጣ ፣ የሚሰማው አጣ ።

ዛሬ ሀገራችን የገባችበት መከራ ምንጩ ፣ የስድ ጓዶች ፣ የመሃይም ጀነራሎች ፣ የባለጌ ሚንስትሮች ፣ የዱርዬ ጳጳሶች እና የወሮበላ ዳኞች ሀገር ስለሆነች ነው ። ባለጌ ብልግናው እሱ ጋ አይቆምም ፣ የ ባለጌ ትውልድ አባወራ ፣ የባለጌ ልጆች አባት ፣ የባለጌ ስርዓት ባለቤት ይሆናል ። ለዚህም ነው ባለጎችን የሚያግባባቸው እና የሚያመሳስላቸው ነገር ሁሉም አለመግባባታቸው ነው የሚባለው ። በባለጌ ስርዓት ውስጥ ይሉኝታ የለም ፣ ሰው ምን ይለኛል የለም ፣ ሀፍረት የለም ፣ ክብር የለም ፣ ታሪክ የለም ፣ ሕዝብ የለም ፣ እምነት የለም ፣ ነገ የለም !

ሕፍረቱን ያጣ ስርዓት ፣ ስርዓቱን የተነጠቀ ሕዝብ ፣ ጨዋነት የራቀው መንግስት ፣ የመዋረድ እና የማጎብደድ ርካሽነት የሚያይበት አእምሮም ነብስም የለውም ። ስለዚህ በሊቢያ መታረድም ሆነ በሱማሊያ ጦር መማገድ ሃገራዊ ውድቀት ሳይሆን እንደ አንድ የማህበረሰብ የለት ተለት ተራ ክንውን ተደርጎ የሚወሰደው ።

ድርቅ አሳሳቢ የተፈጥሮ ቀውስ ነው ፣ ረሃብ አሳዛኝ ዕጣ ፈንታ ነው ፣ ሞት የዚህ አሳዛኝ ዕጣ ፈንታ መቋጫ ነው ። ባለጌ ስርዓት ፣ መሃይም መንግስት ፣ ዱርዬ አስተዳደር እነዚህ ጉዳዮች እንደ ሃገራዊ ጉዳይ ሳይሆን እንደ ጠላ ቤት አምባጓሮ ነው ሊፈታቸው የሚያስበው ፣ የዚህም ሁነኛ ማሳያ በኮረም የቤት እመቤቷ ወይዘሮ ብርቱካን ልጇን በረሃብ እንድተነጠቀች የ ቢቢሲ ( BBC ) ዜና ጣቢያ መዘገቡን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ( በባለጌዎች የሚመራ ባለጌ ተቋም ) ይህችን ሴትዮ ያለችበት ድረስ በመሄድ ፣ ልጇ የሞተው በረሃብ እንዳልሆነ እንድትናዘዝ አድርገዋታል ። በግድ ይቅርታ ሲያስጠይቁ እና ሲያሸማቅቁ ይህች ሴት ሁለተኛዋ ብርቱካን መሆኗ ነው ።

አሳፋሪ ነው ! ህሊና የሌለው ባለጌ ስርዓት ይህንን ያደርጋል ፣ በለስ ሲበላ ያደገ ለማኝ ወታደር ፣ ስልጣን ሲይዝ በረሃብ ይቀልዳል ፣ በተራበ ይቀልዳል ፣ ረሃብ በነጠቀው ሰው ይቀልዳል ። ምክንያቱም አስተዳደጉ ፣ ባህሉ ፣ የሕይወት ተመክሮው ፣ ማንነቱ እና የዛሬ ምንነቱ ባንድ ላይ በብልግና ላይ የተመሰረቱ ስለሆኑ ፣ በዘለፋ እና በንቀት ፣ በጉራ እና በሴስ ፣ በሱስ እና በስርያ ማንነቱን የተረጎመ ጥርብ ባለጌ ስለሆነ ፣ የሰው ነገር ፣ የሀገር ነገር ፣ የጨዋ ነገር ፣ የነገ ነገር የሚባል አንዳችም ነገር በደሙ ውስጥ የለም ። ባለጌን በሃሳብ አታሸንፈውም ፣ ምክንያቱም ማሰብ እን አሃሳብ አያውቅም ፣ ለያንዳንዱ ሃሳብህ እኩሌታ ስድብ ፣ እኩሌታ ብልግና ፣ እኩሌታ ነውር እንደ መልስ ያቀርብልሃል ። ምክንያቱም መባለግ ባህሉ ነው ፣ ነውር ወይም ጸያፍ የሚባል ነገር ሲያድግ አያውቅም ፣ እያደገ አያውቅም ፣ ካደገ ወዲያም አያውቅም ። እንደ አረም ጫካ ውስጥ ተፈጥሮ ፣ እንደ ብልቃጥ በየከተማው ቦይ እና መሸታ ቤት የሚንጫጫ፣ የሚጮህ ፣ የምያቃጭል ፣ ነውረኛ እና ስድ አደግ ስለሆነ ።

ዛሬ መሪዎቻችን ባለጌዎች ናቸው ፣ ባለጌ የወለዳቸው ነው ፣ ባለጌ ልጆች በተራቸው የወለዱ ናቸው ። ዛሬ በየ ሺሻ ቤቱ ፣ በየ ሀሺሽ መሸጫው ፣ በየ ገላ መነገጃው ውስጥ ፣ ደላላው ፣ ተጠቃሚው ፣ አስተናባሪው እና አቀናባሪው አባት እና ልጅ ናቸው ። ሀፍረተ ቢስ እና ርካሽ መሪዎች! ባለጌ እና የነውረኛ ልጆች !

ሃዋርድ ዝን የተባለ ታዋቂ የጥበብ ሰው ” All protest literature says to the reader , “ have hope you are not lone “ “ ማለት ነው ሲል ይገልጸዋል ።
ልዋሰው

All vagabond fathers, all vulgar fathers and corrupted systems are telling the corrupter and the corrupted that “ have hope you are not alone “ ነው የሚለው ።

መደምደሚያ
በከሸፈ ትውልድ መሃል እንደ ሻማ የሚቀልጡ አባቶች ስላልነሳን ፣ እኛ ግን ጠፍተን አንጠፋም ። ለመንገዳችን ብርሃን ፣ ልልባችን ተስፋ የሚሆኑ እና የሆኑ ስል እና ብስል አባቶች ስላሉን ፣ እኛ ግን አንወድቅም ! ተስፋችን ፣ በገለባ ሕልም ጉብ ያለ ራእይ አይደልም ፣ እኛነታችን በአምካኝ ብኩን ወጠጤ ፣ በከሸፈ ጥርብ መሃይም ፣ መሃይምነቱን በወረሰ ዘላን ጎረምሳ የሚዳፈን አይደለም ። እኛ ኢትዮጵያውያኖች ነን ፣ ኢትዮጵያዊነታችን ደሞ ኃይል ነው ፣ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያለውን ኃይል ባለጌ መሪ አያከሽፈውም ፣ አያሸንፈውም ፣ እንደውም ጫፉን አይነካውም ። እንደነሱ ጭካኔ እና አውሬነት ቢሆን ዛሬ እኛ ዱዳ ፣ በድን እና ምውት መሆን ነበረብን ፣ ግን ዛሬም የምንተነፍሰው ፣ ዛሬም ቀና ብለን የምንሄደው ፣ ዛሬም ለለማኝ እና ለሰሃን አጣቢ ፣ ለጩሎ እና ለእንቁላል ተሸካሚ ያልተንበረከክነው ኢትዮጵያዊያኖች ስለሆነን ነው !

እነወጣለን ፣ ከቆረጥን ይህንን ባለጌ እና ነውረኛ ስርዓት መጣል እንችላለን ። በደማችን የያዝነው ማንነታችን በደማቸው ከያዙት ርካሽነት እጅግ የተሻለ ነውና ፣ እንበርታ !
ባለጌ እና ስልጣን ጥፋት ስለመሆናቸው አንርሳ ! ከባለጌ ወታደር ፣ ከዱርዬ መንግስት ፣ ከሸቃይ ሚንስትር ምን እንጠብቅ ?!