ወንጌል እና ሰይጣን፣ ትግሬ እና ብርቱካን ( ሄኖክ የሺጥላ )
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ወንጌል እና ሰይጣን፣ ትግሬ እና ብርቱካን ( ሄኖክ የሺጥላ )
የብርቱካን አሊ ልጅ አብዱ በራ’ብ እንዳልሞተ ወያኔ ነገረን ። በዛ ላይ ቢቢሲ ደሞ እንደ ኢሳት እንደዋሸ ተነገረን ። ይሁን !
እንበልና የብርቱካን ልጅ በራብ አልሞተም ፣ ቀጥሎም የብርቱካን ልጅ በቁንጣን ነው የሞተው እንበል ፣ እንደውም እንደ ወያኔ ባለ ስልጣን ልጆች ሰክሮ መንገድ ላይ ውስኪ እየደፋ ሲሄድ የደፋው ውስኪ አዳልጦት ነው የሞተው እንበል ፣ ከፍ ሲል ለቢቢሲ ጋዜጠኛ ያሳየችው ቅጠል የተሸፈነ የልጇ የአብዱ መቃብር ሳይሆን የእህል ማስቀመጫ ጎተራ ነው እንበል ፣ እነዚህ ሁሉ እውነት ሆኑ እንበል ፣ ከዚያስ ?
እርግጥ ነው ፣ ነገሩን በጥልቀት ከተመለከትነው የብርቱካን ልጅ የሞተው በራብ አይደለም ፣ ራብ ነብሱን ከስጋው የለየው የመጨረሻው ጉዳይ ይሆን ይሆናል እንጂ ፣ የብርቱካን ልጅ የሞተው ፣ እኛ ወንድነታችንን የተቀማን ግዜ ነው ፣ ብርቱካን ልጆቿን የቀበረችው የወለደቻቸው ቀን ነው ፣ እርግጥ ልጇን አፈር ያለበሰችው ዛሬ ነው ፣ መቃብሩ የተቆፈረው ግን ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ ነው ። ረሃቡ ሞትን ያስከተለ አንድ ምክንያት ሊሆን ይችላል እንጂ የብርቱካን ልጅ ረሃብ ባይኖርም አያድግም ! ሰው አይሆንም ! ሃገሩን አይጠቅምም ! ባገሩ አይጠቀምም !
የብርቱካን ልጅ አድጎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ረሃብ ነብሱን ከቀማው የተለየ ነገር አይጠብቀውም ነበር ። ወይ የባህር ውሃ ይበላዋል ፣ ወይ የሱማሊያ ወታደር ሆኖ የፈንጅ ማምከኛ ይሆናል ፣ አልያም በየ አረብ ሃገራቱ እንደ አሸዋ ይበተናል ።
ብርቱካን ( በዘንድሮ አስተሳሰብ ትግሬ ባለመሆኗ ብቻ ) አይርባትም ፣ ሊርባት አይችልም ፣ አይጠማትም ፣ ሊጠማት አይችልም ፣ አይቸግራትም ፣ ሊቸግራት አይችልም ። እንደውም ከቆመችው ብርቱካን ፣ ልጇ አብዱ የተሻለ እረፍት ያገኛል ። ብርቱካን እድለኛ እናት አይደለችም ፣ ምክንያቱም ወንድ ልጅ ወልዳ አላሳደገችም ፣ ቀየዋ ወንድ አልወለደም ። ስለዚህ እናቱን ሲንቁበት ፣ እህቱን ሲደፍሩበት ፣ ሃገሩን ሲቀሙት ፣ ዝም ያለ ትውልድ ፣ የ አልቃሻ እና ሆደ ባሻ ወንድ ዘመን እናት ነች ። ስለዚህ አይደልም ልጇ አብዱ ብርቱካን ራሷ ሙታለች !
እኔ ትግሬ ነኝ ወያኔን ግን አልደግፍም ባይ መጻጉ ፣ ልበ እባብ አፈ ቀላጤዎች ፣ እንደዚህ አይነት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ባንድ ኢትዮጵያዊ እናት ላይ ሲፈጸም < ልክ አይደለም አላሉም !> ፣ ትናንት ወያኔ ወንዝ ውስጥ ወርውሮን ከሞት ተርፈን በህንድ አርገን ፣ በእንትን አርገን አማሪካ ገባን የሚሉት ሳይቀሩ ፣ ደማቸውን ቆጥረው ፣ ማንነታቸውን ቆንጥረው ፣ ስለዚህ ጉዳይ አንዳች ነገር ሲተነፍሱ አታዩም ። የድህረ ገጽ ባለቤቶቹም ፣ ከሞተ 15 ዓመት የሆነውን ሰው ታሪክ አንስተው < ክንፈን መለስ ገደለው > አከሌ በደለው ይሉናል ፣ ለምን መሰሪዎች ስለሆኑ ! ለምን የብርቱካን መሞት ለነሱ ምናቸውም ስላልሆነ ፣ ለምን ብርቱካን መሞት ስላለባት !
መደምደሚያ
አብዛኛውን ጊዜ ስለ ትግሬ መክፋት ሳወራ ወገቡን ይዞ የሚከራከረው አማራ ይገርመኛል ። ቢያንስ ስለ ብርቱካን ስትሉ ዝም በሉ !
ግራህን ሲመታ ቀኝህን ስጣቸው የሚለው ትምህርት የተሰበከበት ሀገር ሰዎች ፣ ስለ ማንነታቸው ምን እንደሚያረጉ ማን አያውቅምና !
የ ሴፕቴምበር 11ን’ አደጋ ተከትሎ አማሪካኖች ለኢራቅ ግራ ጉንጫቸውን ሰጡ እንዴ ? ታዲያ የኛ ክርስቶሳዊነት ምንጩ ምን ይሆን ?
የጋራ ሀገር ሳይኖር የጋራ ፍቅር የሚባል ነገር የለም ። የብርቱካን ልጅ በራብ ሞቶ ፣ የ አዜብ መስፍን ልጅ ጠግቦ የሚያድርበት አንዳችም ሰማያዊ ምክንያት ስለሌለው ግራዬን ሲመቱኝ ፣ የሚዞር ቀኝ ጉንጭ የለኝም ! ለሰይጣን ወንጌል የምናስተምር ባንሆን እላለሁ !
