ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች በሊቢያ ከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ናቸው ሲል የመንግስታቱ ማህበር ገለጸ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወደ አውሮፓ ተሻግረው ለተሻለ ኑሮ በሚል ተስፋ ሰንቀው በሊቢያ ውስጥ የሚገኙ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሊቢያ በከፍተኛ ችግር እና ሰቆቃ ውስጥ ናቸው ያለው የመንግስታቱ ማህበር ሕገወጥ የሰው ደላሎች ከፍተኛ ግፍ እየፈጸሙባቸው መሆኑን በአመታዊ ሪፖርቱ አስቀምጧል:: ሪፖርቱ እንዳለው ስደተኞች ጥገኝነት ፈላጊዎች በተለህ ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት የሚሰደዱ በሊቢያ ውስጥ እንደሚገደሉ ከሰብኣዊነት ውጪ ግፍ እንደሚፈጸምባቸው እደሚደፈሩ ገንዘባቸውን በታጣቂዎች እንደሚዘረፉ እንደሚታገቱ እና ገንዘብ እንደሚጠየቅባቸው የመሳሰሉት ሰቆቃ በሕገወጥ ተሰው አዝዋዋሪ ደላሎች እንደሚፈጸምባቸው ተረጋጧል::

አብዛኛዎቹ ተጠቂዎች ለዚህ ችግር የሚጋለእጡት ድላሎቹ በሚወስዷቸው የሊቢያ መንገዶች ላይ ሲሆን ሕገወጥ ደላሎቹ ለተጓዦች ችግር መንስኤ ናቸው ሲል የመንግስታቱ ማህበር በሊቢያ የሚገኘውን የድጋፍ ቢሮውን እና የሰብኣዊ መብት ቢሮን ዋቢ አድርጎ አስቀጧል::
ተጓዦች ከመንገድ ላይ በታጠቁ ሃይሎች በሕገወጥ ደላሎች ትብብር ይታፈኑና ታግተው ከተጓዥ ቤተሰቦች ገንዘብ ለማግኘት መደራደሪያ እንደሚደረጉ ሪፖርቱ ጠቅሶ የተቀናጁ እና የተደራኡ የወንጀል ሃይሎች በሊቢያ ውስጥ ከሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪ ደላሎች ጋር ይህንን ይፈጽማሉ ሲል ማህበሩ ተናግሯል::ሴቶች በጭለማ ተወስደው ይደፈራሉ ይነወራሉ ሲል ሪፖርቱ አክሏል::

በትሪፖሊ አከባቢ የስደተኞች ማረፊያ 5000 ስደተኞች ሲገኙ የሰሜን አፍሪካ አገራት ለስደተኞች ወደ ዐውሮፓ ለመሻገር መንገድ የሆኑ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሊቢያ ያለው አለመረጋጋት የጠቀማቸው ሕገወጥ ደላሎች የተለያየ የወንጀል ቡድን በመፍጠር በተጓዥ ስደተኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ በደል እና ግፍ እየፈጸሙ ይገኛሉ::

Image