ለራስዋ ያላወቀች ለቅዱስ ገብርኤል መድሃኒት ጠየቀች::የፓሪሱን ጥቃት የረሃቡን ጉድ ለመሸፈን አጀንዳ ማድረግ ዝቅጠት ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi – አንድ – ለፓሪሱ ጥቃት አስለቃሽ የተቀጠሩ ይመስል የወያኔ ካድሬዎች ሙሾውን ተያይዘውታል::የኢትዮጵያ ረሃብ ሕዝብን እየገደለ እያሳደደ ባለበት በዚህ አደገኛ ጊዜ ላይ የድርጊት መረሃ ግብሮች ሁሉ ሕዝብን ለማዳን መረባረብ በሚጠበቅበት ወቅት የፓሪሱን ጥቃት እንደ አጀንዳ ይዞ ማራገብ አገዛዙ ምን ያህል የዘቀጠ እና መቀበሪያው የደረሰ መሆኑ ያሳያል::

ሁለት – ለእርዳታ በተሰማሩ የውጪ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ደህንነት መላክ ማሳቀቅ እና ማስደንበር ምን አመጣው? ረሃብ የለም ብላ ወያኔ ሰውን ለማሳመን በምትቧጥጥበት ሰአት ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰባዊ ጉዳዮች ቢሮ ያሰባሰባቸው የተለያዩ የእርዳታ ድርጅት ስር ያሉ ኢትኦጵያውያን ስራቸውን መስራት አለመቻላቸውን ከሰሜን ኢትዮጵያ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ::ድንጋጤያቸው እኮ የሚጨብጡት የሚይዙት ሁሉ እሳት ሆነባቸው የገዛ ስራቸው ፈጃቸው::

ሶስት – ባለስልጣናት የእርዳታ እህሎችን እና ቁሳቁሶችን ካላስረከባችሁን እያሉ በጎን ለማስማማት ይሞክራሉ የሚባለውን ሌላው መረጃ ነው::እርዳታውን ተረክበው በመሸጥ የግል ኪሳቸውን ለመሙላት የሚሯሯጡ ባለስልጣናት የፖለቲካ ትርፍ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ትርፍም ለማግኘት የሚሮጥ በሞላበት አገዛዝ ምን ያህል ወገን አደገኛ ችግር ውስጥ እንዳለ ልንረዳለት ይገናል::

አራት – ስለ ወገን ስለ ሃገር ሲባል የበጎ ፈቃደኝነት ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ ጀምሯል::ይህንን ለመርዳት የምትፈልጉ ሁሉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ የባንክ ሒሳብ ቁጥር (1000143645987) ተከፍቷል፡፡ ስለዚህ ወገን ለወገን ነው እና ከ100 ብር ጀምሮ የተቻላችሁን ሁሉ በአካውንት ቁጥሩ በማስገባት ወገንን እንድረስለት ::ወገን ለወገን!!!

Minilik Salsawi's photo.