በፈረንሳይ ፓሪስ የአጥፍቶ ጠፊዎች እና የታጣቂዎች ጥቃት ከባድ ጉዳት አደረሰ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የፓሪስ ከተማ ፍንዳታዎች አለምን አስቆጥቷል አስደንግጧል::እስካሁን 158 ሰዎች ሞተዋል::በአጥፍቶ ጠፊዎች የቦምብ ጥቃት እና በታጠቁ ሃይሎች የደረሰው ግድያ ፓሪስን አናውጧታታል::የፈረንሳይ ፕሬዚዳት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያውጁ የፈረንሳይ ድንበሮች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል::
በስታድ ደ ፍራንስ ስታዲየም አቅራቢያ በተዘጋጀ የሙዚቃ ኮንሰርት በተፈጸመ ሽብር ነው ጥቃቱ የተፈጸመው።ባታክላን በተሰኘው አዳራሽ ውስጥ በተዘጋጀው የሙዚቃ ድግስ ላይ ታጣቂዎች ድንገት በመግባት ታዳሚዎችን አግተዋል። በዚህም 80 ሰዎችን በመተኮስ መግደላቸውን ነው ከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያመለከቱት።በአጠቃላይ ስድስት ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን፥ ተከታትለው በደረሱ የቦንብ ፍንዳታዎች ንፁሃን ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል።በስፍራው የጸጥታ ሃይሎች ከደረሱ በኋላ በተደረገ የተኩስ ልውውጥም ታጣቂዎቹ መገደላቸውን የፈረንሳይ ፖሊስ እየገለጸ ነው።