አርቲስት ደበበ እሸቱ “the Golden Leopard award” የምርጥ ተዋናይ “Best Lead Actor” የሚለውን ዘርፍ ተሸላሚ ሆነ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

አርቲስት ደበበ እሸቱ ዛሬ በካናዳ ቫንኮቨር በተካሄደው “the Golden Leopard award” በሚል የሚጠራው እና በሰሜን አሜሪካ መልቲ ካልቸራል አለምአቀፍ የፊልም ሰሪዎች ማህበር የሚያዘጋጀው ስነስርዓት ላይ “ቀያይ ቀምቦጦች” “עלים אדומים Red Leaves” በሚለው ፊልም መሪ ተዋናይ ሆኖ ባሳየው ብቃት የምርጥ ተዋናይ “Best Lead Actor” የሚለውን ዘርፍ አሸናፊ በመሆን በተወካዩ አማካኝነት ሽልማቱን ተቀብሏል፡፡


Red Leaves ፊልም በአሁኑ ሰዓት በበርካታ ሀገሮች ታላላቅ የፊልም ፌስቲቫል ላይ እየታየ እና ከፍተኛ አድናቆት እየተቸረው ሲሆን በተለይም የመሪ ተዋናዩ ደበበ እሸቱ ብቃት በአለም አቀፍ የፊልም መድረክ ላይ ተመልሶ ያንጸባረቀበት እንደሆነ እየተገለጸ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ሰዓትም “ቀያይ ቀምቦጦች” ፊልም በአውስትራሊያ፣ በጀርመን፣ ሳንፍራነሲስኮ፣ በማንሀታን ኒውዮርክ፣ በለንደን እና በርካታ ከተሞች ላይ እየታየ ይገኛል፡፡
አርቲስት ደበበ እሸቱ እንኳን ደስ ያለህ ፡፡