ሩስያ 11 000 ዜጎቿን ከግብፅ አስወጣች:: ወደ 70ሺህ የሚጠጉ ይቀራሉ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሩስያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ግብፅ ውስጥ የሚገኙ 11,000 ሀገር ጎብኚ ዜጎቿን አስወጣች። ዛሬ እሁድም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አርካዲ ድዎርኮቪችን ዋቢ አድርጎ የሩሲያ ዓለም አቀፍ የዜና ኤጀንሲ (RIA) ዘግቧል።

እንዲሁ 2000 የሚጠጉ የብሪታንያ ሀገር ጎብኚዎች ከግብፅ ሻርም ኤል ሼህ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ዛሬ ተዘግቧል።

ግብፅ ውስጥ ከደረሰው የሩስያ የአውሮፕላን አደጋ በኋላ ሩስያ የግብፅ ሙሉ በሙሉ በራራዎችዋን ላልተወሰነ ጊዜ በመሰረዟ ምክንያት 80,000 የሚጠጉ ሀገር ጎብኚ ዜጎቿ መመለሻ አጥተው ግብፅ ውስጥ ነበሩ።

[youtube http://www.youtube.com/watch?v=BtHyMhGWCxg]