ተዋናዮቻችንና አለባበሳቸው : Melkam-selam Molla (Ethiopian Movie)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በቀን 24 ትርፍ ሰዐት ስላለኝ youtube ጋር የወጡትን አብዛኛውን የሀገሬን ፊልሞች አይቻለሁ ። እንዴት ነው አዲስ አበባ የሚኖሩ እንስቶች ቲሸርት ብቻ ለብሰው መውጣት ጀመሩ እንዴ? መቸም ያን ቀሚስ ነው ማለት ይከብዳል ። ወይ ካሜራው ረዘም ያለ ቀሚስ ሲሆን ምስሉ አይገባለትም ይሆን:-P ዳይሬክተሮቻችን አጭር ቀሚስ ያለበሰች ተዋናይት ‘ቀሽም ‘ ናት ብለው ማሰብ ጀመሩ እንዴ። በዛ ላይ ቁጭ ሲሉማ አይነሳ።ጥበብ የአንድ ሀገር ባህል ፡ ኑሮ ፡አስተሳሰብ ወ.ዘ.ተ ነፀብራቅ ነው ። አለባበሳቸው የኢትዮጵያ ባህል የሚወክል ሳይሆን የሚያጠፋ ነው ። ኸረ ሴቶቻችን፡ ዳይሬክሮቻችን ይደብራል። ሁለት ፖንት አንድ ቀሚስ መሆን ጀመረ እንዴ:
እግረመንገዴን ደሞ እስኪ ልደት የሌለበት ፣ወንዱ ዋሽቶ ሴቱዋ ውሸት የማትወድ ፡ ተዋደው ተጣልተው ከዛ ተገናኝተው የማያልቅበት፡ ሀብታም ቤት ፡ እኔ ነኝ ያለ መኪና ስልክ የሌለበት፡ ሁሌ የገጠር ሰዎች ሰራተኛ ሆነው የማይሰሩበት፡ ልጅ እናት እና አባታቸውን ጮኸው የማይናገሩበት፡ሁልጊዜ ቆንጆ ቆንጆ ተዋናዮችን ብቻ የማናይበት፡ሲጋራ የማይቦንበት፡ውስኪ የማይራጭበት፡ሴቶች የማይሞላቀቁበት……ፊልም አሳዩን። ታክሲ ወረፋ ሲጠብቅ ፡ስኳር ጠፍቶ በጨው ሲጠጣ፡ድሀና ድሀ ሲፋቀሩ ምናምን አሳዩን።

Melkam-selam Molla's photo.