መንግስታዊ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች በገንዘብ የታጀቡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi's photo.

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የሕወሓት/ኢሕኣዴግ ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በገንዘብ የታጀቡ ናቸው፡፡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ሕገወጥ ገንዘብና ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሕግን ከመጣስና ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌላውን አስወግደው እነሱ ብቻ የሚቆጣጠሩትና የእነሱን ፍላጎት ብቻ የሚያረካ መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!፡፡ ጉዞው ሌቦች የበላይነት የያዙበትና የሌቦች መንግሥት የተቁዋቁዋመበት ነው!!!

የተወገዘ የነበረው የተለመደ ሆኗል፡፡ ጉቦ መውሰድ ኃጢአትና ወንጀል መባሉ ቀርቶ ጉቦ አለመቀበል ጅልነትና ሞኝነት እየተባለ ነው፡፡ፀረ ሕዝብ፣ ስስታም፣ ስግብግብና በሙስና የተጨማለቁ ለግል ጥቅምና ክብር ሲሉ አገርንና ወገንን ከመሸጥ፣ ከመለወጥ፣ ከመካድና ከመርገጥ ወደኋላ የማይሉ ባለሥልጣናት በሥልጣን ላይ መቀመጥ የሌለባቸው፣ መሾምና መከበር የማይገባቸው ባለሥልጣናት እንደዚህ ዓይነት ባለሥልጣናትና ሹሞችን ይዞ አገርን ከአደጋ ማዳን፣ ሕዝብን ከድህነት ማላቀቅና ፍትሕና ዴሞክራሲን ማስፈን አይቻልም፡፡

ይህን ሕዝብ ከድህነት ማላቀቅና ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን የሚሆነውና በተግባር የሚታየው፣ ሀቀኖቹ በሌቦቹ ላይ የበላይነት ሲያረጋግጡ ብቻ ነው፡፡ በተግባር ሀቀኞች በሌቦች ላይ የበላይነት ሊኖራቸው የሚችለው ደግሞ ሲታገሉና በትግሉም ዋጋ መክፈል ሊኖርባቸው እንደሚገባ አምነው ሲንቀሳቀሱ ብቻ ነው፡፡
በቃል፣ በንድፈ ሐሳብ፣ በመግለጫና በቃለ መጠይቅ የመንግሥት ሌቦች እንዳሉ መናገሩና ማውገዙ ብቻ የትም አያደርስም፡፡ እንቅፋት ናቸው ብሎ መግለጹ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የመንግሥት ሌቦች ካልተወገዱ የሌቦች መንግሥት ይመሠርታሉ ብሎ ማመን፣ ይህ የሌቦች መንግሥት እውን እንዳይሆን ለመቅጣት፣ ለማስወገድና ለመጠራረግ ቆራጥ ትግል ያስፈልጋል፡፡

ሌቦችን ለማስወገድ ተቸገርን ብለው ሊያማርሩ አይገባም፡፡ ሊጨነቁ አይገባም፡፡ችግር የለም ነገ ከነገ ወዲያ እናስወግዳቸዋለን ተብሎ የሚተው ጉዳይም አይደለም፡፡ ሀቀኛው በተዝናና ቁጥር ሌባው እየተጠናከረ ይመጣል፡፡ በገንዘብ ተከታዩን ይገዛል፡፡ በገንዘብ ኔትወርክ ይዘረጋል፡፡ በገንዘብ ከውጭ ጠላት ጋርም ሊተሳሰር ይችላል (ሌብነት ድንበር የለሽ ነውና)፡፡ በገንዘብ ሀቀኞችን የሚያስወግዱ ኃይሎችን በማሰማራት ሊያሸንፍ ይችላል፡፡ በገንዘብ የመገናኛ ብዙኀንን ሊቆጣጠር ይችላል፡፡አቅም ያጣውን፣ ዕውቀትና ልምድ ያነሰውን በትምህርትና በሥልጠና ማጠናከር ይቻላል፡፡ ሌባና ወንጀለኛን ግን የሥልጠና፣ የሴሚናርና የውይይት ብዛትና ዓይነት አይለውጠውም፡፡ ሕጋዊ ዕርምጃ ብቻ ነው መፍትሔው፡፡በከፍተኛ የአገር ኃላፊነት በመንግሥት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን ማጥራት ነው፡፡ የሕዝብ፣ የአገር፣የዴሞክራሲ፣ የፍትሕና የሰላም ጠላቶችን ማስወገድ ነው፡፡ ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬