በደቡብ አፍሪካ ስድስት ኢትዮጵያውያን ተገደሉ::ደቡብ አፍሪካውያን ለውጪ ዜጎች ያላቸው ጥላቻቸው አገርሽቶባቸዋል::‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ከደቡብ አፍሪካ ደርባን የአይን እማኞችን ጠቅሶ የአሜሪካ ድምጽ እንግሊዘኛው ድህረገጽ እንዳለው ባለፈው ሳምንት ብቻ ስድስት ኢትዮጵያውያን የውጪ ዜጎች ይውጡልን በሚሉ ደቡብ አፍሪካውያን መገደላቸው ታውቋል::ዮናስ ፍቅሩ ይባላል በደርባን ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ሲሆን ስድስቱንም ሟጮች ያውቃቸዋል::ሁሉም በ20ዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ናቸው::እጅግ በአሰቃቂ ሁኔታ በደቡብ አፍሪካውያኑ በጠራራ ጸሃይ እንደተገደሉ ተናግሯል::ምም የዘረፉት የለም መተው በቀጥታ ገለዋቸው ሄደዋል ሲል ለምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ተናግሯል::

ተገኔ አቦዬ የሚባል በደርባን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባል ሁኔታውን በተመለከተ ለፖሊስ ሪፖርት ብናደርግም ፖሊስ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል::አይሰማንም ሲል ተማሮ ተናግሯል::ገዳዮቹ በአገራችን የፈለግነው የማድረግ መብት አለን የሚሉ ሲሆኑ በየጊዜው ዘረፋ እና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን በውጪ ዜጎች ላይ ይፈጽማሉ::የኢትይኦፓያ ኤምባሲ ምንም ትብብር ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም ሲል ተገኔ ይናገራል::

ወንድሞቻችን ተገለው አይተናል::በሶስት ሊትር ነሽ ጋዝ ተደፍቶባቸው ተቃጥለዋል::ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ማንም የሚረዳን የሚያድናቸውም አላገኘንም ሲል የሚናገረው ኢትዮጵያዊው ተገኔ ለኢትዮጵያውያን የሚከራከር ይሁን ጥቃቱን የሚከላከልላቸው እስካሁን አላየንም ሲል ገልጿል::የአሜሪካ ድምጽ የደርባንን ፖሊስ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም::ከጥቂት አመታቶች በፊት ጀምሮ ደቡብ አፍሪካውያን የውጪ ዜጎች ይውጡልን በሚል ጥላቻቸው እየገለጹ ሲገኙ ጥላቻውን እስከ መግደል ማቃጠል እና መዝረፍ ዘልቋል::ደሃ የሚባሉት አብዛኛው ደቡብ አፍሪካውያን ስራዎቻችንን የውጪ ዜጎች ተቆታጥረውታል ሲሉ የውጪ ዜጎችን ወደ ማጥቃት ወንጀል አምርተዋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬