በደቡብ ምስራቅ እዝ ያለው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥለው መኮብለላቸውን ቀጥለዋል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 

Minilik Salsawi – በሰራዊት ውስጥ ያለውን የአንድ ዘር የበላይነት የፖለቲካ ነጻነት አለመኖር የጥቅማጥቅም ጉዳዮች የደረጃ እና የማእረግ እድገት ማጣት በሶማሊያ ስለዘመቱት ወታደሮች ጉዳይ ከየክፍላቸው እየታፈኑ ስለሚታሰሩ እና ስለሚሰወሩ የሰራዊት አባላት ጉዳይ ከፍተኛ ተቃውሞ ከሚያሰሙት ከመከላከያ እዞች አንዱ የሆነው በጄኔራል አብርሃ የሚመራው የደቡብ ምስራቅ እዝ የሰራዊቱ አባላት ሃገር ጥለው ወደ ባሌ ጫካዎች እና ወደ ኬንያ መኮብለላቸውን ቀጥለዋል::

Minilik Salsawi's photo.

በሰራዊቱ እስጥ ያለ አለመግባባት እና ችግር እንዳይፈነዳ ወያኔ በከፍተኛ ጥንቃቄ አፍኖ ይዞታል የሚሉት የመረጃ ምንጮች የሆኑት ከፍተኛ ወታደራዊ ደህንነቶች ለምንሊክ ሳልሳዊ እንደገለጹት የታሰሩትንን እና በጋንታ መሪዎች የተሰወሩትን ሳይጨምር ባለፉት ሁለት ወራት ባቻ ቁጥራቸው ወደ 500 የሚጠጉ የሰራዊት አባላት ጠፍተው ወደ ጎረቤ አገር ኬንያ እና ወደ ባሌ ተራሮች ጫካ መግባታቸውን ጠቁመዋል::

በስሜን እዝ ካለው አፈና በተለየ ሁኔታ ነጻነታቸውን አጥተው እየኖሩ ያሉት የደቡ ምስራቅ ሰራዊት አባላት የወያኔ መንግስት ለፕሮፓጋንዳ ከሚጠቀመው ዲስኩር በተቃራኒው ያለው እውነታ እጅግ አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ሲሆን የሰርዊቱ አባላት በረባ ባረባው እየታፈኑ ከመታሰር ጀምሮ እስከ መሰወር እንደሚደርሱ ወታደራዊ ደህንነቶቹ ይናገራሉ::የሰራዊቱ አባላት ተንካራ እና የፖለቲካ ለውጥ ያመጣል የሚሉት አስተማማኝ ለመስዋትነት የተዘጋጀ አስተባባሪ የፖለቲካ ድርጅት ማጣታቸው እንጂ በአጠቃላይ የወያኔን አገዛዝ ከመግዳት የማይመለሱ የተዘጋጁ መሆኑን አክለው ተናግረዋል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬