ሞቃዲሾ ሁለት የቦምብ ፍንዳታዎች አስተናገደች::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


#SahafiHotelAttack #Mogadishu – በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በአንድ ሆቴል ደጃፍ ላይ በመኪና ላይ የተጠመደ ፈንጂ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል::ይህንን ተከትሎ ወደ ሆቴሉ ሕንጻ ለመንባት በሞከሩ ታጣቂዎች እና በመንግስት ሃይሎች መካከል በተፈጠረ የተኮስ ልውውጥ በርካታ አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በድጋሚ የቦንብ ፍንዳታም ተከስቷል::አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳሉት በሆቴሉ ውስጥ ከነበሩት የፓርላማ አባላት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ያረጋገቱ ሲሆን እንደ ሮይተር ዘገባ በሆቴሉ በር ላይ በመኪና ላይ ተጠምዶ በፈነዳው ቦምብ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል::

At least two people have been killed after a car bomb exploded at the gate of a hotel in the Somali capital Mogadishu.
የቦምቡ ፍንዳታ የተከሰተው ያልታወቁ ታጣቂዎች በሳሃፊ ሆቴል አከባቢ የነበረ የፖሊስ አባል ሁለት ንጹሃን ሞተዋል ሲል መረጃ ሰቷል::ቦምቦ በፈነዳ ሰአት ላይ ታጣቂዎች ከተለያዩ ቦታዎች ፖሊሶች ላይ ቶክስ መክፈታቸውም ፖሊሱ ጨምሮ ገልጿል::በሆቴሉ ውስጥ ከነበሩት ከፍተኛ ባለስልጣና አንዱ የሆኑት ጄኔራል አሊ አራያ ጋማዱሌ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን ወዲያው ከቀሪ አደጋዎች ለማምለጥ ችለዋል::ሁለተኛው ፍንዳታ የተከሰተው ከጠዋቱ 6.30 ሲሆን ከመጀመሪያው ፍንዳታ 30 ደቂቃ በኋላ መሆኑ ታውቋል::ከባለስልጣኖች የተረጋገጠ መረጃ ባይገኝም የአልጀዚራ ጋዜጠኛ የአከባቢእ ውማኞችን ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው አምስት ሰዎች ሲሞቱ ከ20 ሰዎች በላይ ተጎድተዋል ብሏል::