የህገ-ወጡ የመጅሊስ አመራሮች በዘንድሮው ሃጅ የፈጸሙት የሙስናና የዝርፊያ ወንጀል ተጋለጠ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የህገ-ወጡ የመጅሊስ አመራሮች በዘንድሮው ሃጅ የፈጸሙት የሙስናና የዝርፊያ ወንጀል ተጋለጠ
ቢቢኤን የእያንዳንዱን የመጅሊስ አመራር በዘመዶቻቸው ስም የፈጸሙትን የሙስናና ዘረፋ ወንጀል በሰነድ ና በፎቶ ግራፍ ማስረጃ አስደግፎ በተከታታይ ለህዝብ ያቀርባል
መረጃ ቁጥር አንድ የህገ-ወጡ መጅሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት ኡመር ይማም የሃጅ የዘረፋ ተግባር የህገ-ወጡ የመጅሊስ አመራሮች በዘንድሮው ሃጅ ላይ በሚስቶቻቸው ፤ በዘመዶቻው ፤ ምንም በማያውቁ ህጻናት ልጆቻቸው ስም በማስመዘገብ ከፍተኛ የዘረፋ ወንጀል መፈጻቸውን ለቢቢኤን በፎቶ ግራፍ ጭምር ተደግፎ በደረሰን መረጃ ተጋለጠ
ምክትል ፕሬዝዳንቱ አህባሹ ኡመር ይመር በሚስቱ፤ ምንም በማያውቁ ሕጻናት ልጆቹ ጭምር ፓስፖርት በማውጣት ለሃጅ የሚሄዱ ናቸው ብሎ በማስመዝገብ በእያንዳንዳቸው ከ32 ሺ ብር በላይ አበል መውሰዱ ታውቋል፡፡ የኡመር ይማም ከታች በመዝገቡ በ105 ላይ እና በፓስፖርቷ ላይ እንደተገለጸው ምንም የማታውቀዋን ታዳጊ ፋኪሃን ለሃጅ የምትሄድ ናት በማለት በስሟ ፓስፖርት በማውጣት የ20 ቀናት አበል በመውሰድ የዝርፊያ ወንጀል በህጻኗ ስም ፈጽሟል
ታዳጊዋ ህጻን በስሟ ወንጀል ተፈጸመባትንጅ ምንም ያደረገችው ነገር ስለሌለ ፎቶ ግራፉ አደብዝዘነዋል
አህባሹ ኡመር ይማም ከዚህ በተጨማሪ በተራ ቁጥር 104 ዘሃራ ኡመር አየለ በምትባለዋ ሚስቱም በተመሳሳይ የሃጅ ሙሉ ነጻ ወጪ እና የ20 ቀናት አበል በመውሰድ የዘረፋ ተግባር መፈጸሙን ቢቢኤን ከውስጥ ምንጮቹ ያገኘው የሰነድና የፎቶ ግራፍ ማስረጃ ያመለክታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ዘመዶቻቸው ፤ ጓደኞቻቸው ስም በማስመዝገብ ከፍተኛ የዘረፋ ወንጀል መፈጸማቸው ታውቋል፡፡ በሃጅ ጉዞ ላይ ኢትዪጲያዊያን ሃጃጆች ለከፈሉበት እንኳን ተገቢውን ግልጋሎት ሳያገኙ ከፍተኛ መጉላላት እንደ ተፈጸመባቸው ይታወቃል፡፡
የህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮች ሙስሊሞችን ለማስጠቃትና ኢስላምን ለማጥፋት በመንግስት አማካኝነት በቦታው ላይ የተቀመጡ ስነ-ምግባር የሌላቸው ግለሰቦች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የሌሎቹንም የዘረፋ ወንጀል በተከታታይ የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
