የወያኔ ዳኞች የአእምሮ በሽተኛ የሆነውን ልጅ የአይሲስ ወታደር ነኝ ብሏል ብለው ሊፈርዱበት ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በባቲ ከተማ የሚገኝ አንድ የአእምሮ በሽተኛ የሆነ ልጅ ከወራት በፊት “አርዳችሃለሁ እገድላችሃለሁ” እያለ ይናገራል። በፌስቡክም ላይ ይፅፋል። እንኳን ዘንቦብሽ እንዲሉ ከፌድራል ቀጥታ ባቲ ድረስ የሄዱ ፖሊሶች ና ደህንነቶች ይህን ልጅ ለመያዝ ባቲ ከተማ ላይ ይደርሳሉ። የአካባቢው ነዋሪዎችም ልጁ የአእምሮ ችግር እንዳለበት ቢናገሩም ቢለምኑም ሰሚ አላገኙም። ከፌድራል የመጣችው መኪና ልጁን ወደ አማኑኤል ሆስፒታል ሳይሆን ወደ ማእከላዊ ይዛው ነጎደች።
የልጁን መያዝ በሰአቱ ቢቢኤን የአካባቢው ነዋሪዎችን በማነጋገር ዘግቦ ነበር።
እነሆ የህወሃት ልሳን የሆነው ፋና ይህን አሳዛኝ ዜና ይዞ ወጣ
እኔ የአይ ኤስ ወታደር ነኝ ባለው የባቲ ከተማ ወጣት ላይ የተመሰረተው ክስ ለብይን ተቀጠረ

-አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት እኔ የአይ ኤስ ወታደር ነኝ በማለት በራሱ የፌስቡክ አድራሻ ህብረተሰቡን አስፈራርቷል በሚል የሽብር ወንጀል የተከሰሰው የባቲ ከተማ ወጣት ላይ የአቃቤ ህግን ምስክር ሰምቶ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ያዘ።

የ31 ዓመቱ ሰይድ መሃመድ ነው የሽብር ወንጀል ክስ የተመሰረተበት።

የፌደራል አቃቤ ህግ ክስ እንደሚያስረዳው ተከሳሹ በስሙ የተከፈተ የፌስቡክ አድራሻ አለው።

ተጠርጣሪው ሚያዚያ 16 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት በቁጥጥር ስር ሲውል በፌስቡክ አድራሻው አይ ኤስ አይ ኤስ ምን መሰላችሁ ልክ እንደኔ በጣም ጨካኝ አረመኔ ነው፤ እኔ አይ ኤስ አይ ኤስ ነኝ፤ የስራ ድርሻዬም ሰውን እጅና እግሩን አንጋልዬ መያዝ ነው፤ የሚለው በፌስቡኩ በቀዳሚነት ለንባብ የበቃ ነው ይላል የአቃቤ ህግ ክስ።
ከዚሁ ሀሳብ ወረድ ብሎ ይህንን በማድረጌ ደመወዝ የሚከፈለኝ በያዝኩት ሰው ልክ ነው የሚል ነው ይላል ክሱ።

እንደ አቃቤ ህግ ክስ ፅሁፉን ተከትሎ የራሱ ፎቶግራፍ ከአንዲት ሴት ልጅ ፎቶግራፍ ጋር ሰፍሮ ይታያል።

እኔ የአይ ኤስ ወታደር ነኝ፤ በቅርቡ ወደ ባቲ ለእርድ እመጣለሁ የሚል መልዕክት በፌስቡክ አድራሻው አስፍሮ በመገኘቱ የፌደራል አቃቤ ህግ የዚህ በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን በመግደል በሚታወቀው የሽብር ድርጅት አባል በመሆን የሽብርተኝነት ተግባሩን ለመፈጸም የተዘጋጀ መሆኑንና ወደ ባቲ በመሄድ የማረድ ተግባሩን እንደሚፈፅም በመግለፅ፣ በመዛት እና በማስፈራራት ለሌሎች የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልእክቱ እንዲደርስ በማድረጉ በፈጸመው የሽብር ድርጊቶችን ለመፈፀም መዛት ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል።

ተከሳሹ ቀደም ሲል በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት ቀርቦ ክሱ ተነቦለት ሰምቶ የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲሰጥ ሲጠየቅ “የቀልድ ነው የፃፍኩት ብሏል”።

አቃቤ ህግ በክሱ ሆን ብሎ ድርጊቱን ፈፅሟል በማለት የመሰረተበትን ክስ ሙሉ በሙሉ ባለማመኑ አቃቤ ህግ ከቆጠረበት እምስት ምስክሮች ሶስቱን እንዳሰማ ሌሎቹ አያስፈልጉኝም በማለቱ ችሎቱ ዛሬ የሰው ምስክሮችን ሰምቶ ማጠናቀቁንና የሰነድ ማስረጃዎችን ተመልክቶ ማጠቃለሉን ተከትሎ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለህዳር 30 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።