71 የኤርትራ መንግስት “የቀይ ባህር ኮርፖሬሽን” ትራከሮች :- በአቶ ስየና በአቶ መለስ ጥልና መቃቃር ትልቁ መነሻ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
1989 ዐም ነው የኤርትራ መንግስት “የቀይ ባህር ኮርፖሬሽን” የሚባል ግዙፍ የንግድ ድርጅተ አቋቁሞ እየሰራ የነበረበት ጊዜ ነው:: በርካሽ ዋጋ ከኢትዮጵያ የተለያዩ የግብርና ምርቶች እየገዛ ለዐለም የሚያቀርብበትና በአጭር ጊዜ በርካታ መቶ ሚልዮኖችን ማንቀሳቀስ የቻለበት ጊዜ ነበር፡፡
ከዚያ አንድ ዐመት ቀደም ብሎ በነበረው ጊዜ ኤርትራ ከዐለም 12ኛ ቡና ላኪ ሆና ኢትዮጵያነ 13ኛ የሆነችበት ጊዜ ነበር:: የሀገሪቱ ሰሊጥም ከገበሬዎች በርካሽ ዋጋ እየገዛ ለዐለም የሚያቀርበው በዋናነት ይሀው ድርጅት ነበር፡፡

በዚያ ጊዜ ህወሐትም ጉና የሚባል የንግድ ድርጅት ኣቋቁሞ እየሰራ ነው የቀይ ባህር ኮርፖሬሽንን ግን መቋቋም የሚችልበት ዐቅምም ብቃትመ ብልጠትም አልነበረውም::
በቀጣዩ ዐመት 1989 ዐም ይህ ደርጅት ከዚያም አልፎ ክረምት እንደገባ በሁመራና መተማ ያሉ ሰሊጦችን ሁሉ ገዛና ጉና አንድ ኩንታል ሰሊጥም ሳያገኝ ቀረ የሆነው እንዲህ ነው: ሰሊጡ ገና እዛው መሬት ላይ እያለና ሳይታጨድ ገበሬዎቹ ዘንድ በመሄድ ነበር የገዛው፡፡
በራሱ ወዛደሮችም አጭዶና ወቅቶ ሙሉውን ሰሊጥ ወሰደው መስከረም ሲጠባ ጉና አንድም ኩንታል ሳይገኝ ቀረ የሆነውም ሁሉ ታወቀ፡፡
በዚህ የተበሳጨው በጊዜው የትእምት/EFFORT የበላይ ሐላፊ የነበረው አቶ ስየ አብርሀ አንድ መላ ዘየደ፡
የኤርትራው የቀይ ባህር ኮርፖሬሽን ድርጅት እራሱ ያጨደውና የወቃው ሰሊጥ ያለምንም የጉምሩክና ሌላ ህጋዊ አሰራር በለመደበት መንገድ ሰሊጡን በራሱ ትራከሮች ሊወስድ መተማና ሑመራ ተመመ:: 71 መኪኖችም ገቡ፡ ተጫኑም:
ይህንን አቶ ስየ እየተከታተለ ነው::
71 ትራከሮች ሰሊጥ ጭነው ድንበር ሲያቋርጡ እንዲያዙ ሆነ::
አቶ ስየ ኤክስፖርት ምርቶችን ያለምንም ሕጋዊ አሰራር መክፈል ያለበት ቀረጥም ሌላም ሳይከፍል ምንም ዶክመንትም ሳያሟላ የሚጓጓዘውን ሰሊጥ እንዲህ ከድንበር እንዲያዝና እንዲወረስ አደረገ፡፡
ይህ አዲስ አበባ አቶ መለስ ዘንድ ተሰማ:: አቶ ኢሳያስን እንደመልዐክ የሚያዩት የነበሩት አቶ መለስ ይህን የሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ: “ልታጣሉኝ ነው ወይ? ተው ስጧቸው” ሆነ::
አቶ ስየ አብርሀ “ህግ ይከበር: እኔ አልመልስም:: በቃ ህገወጥ ነው ተወርሷል” ሆነ::
ይህም በአቶ ስየና በአቶ መለስ ጥልና መቃቃር ትልቁ መነሻ ሆነ፡፡
እዚሁ መቐለና በመላው ሀገሪቱም ስየ አብርሀ 70 ትራኮች አሉት የሚል ወሬ በደህንነት ክፍሉ እንዲሰራጭ ሆነ፣ ፊታውራሪዎቹም ኤርትራውያን ነበሩ(including Bereket, Tesfaye Gebreab)፡፡