ልመንህ በጐዳና…
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ይኖር የነበረው ልመንህ ትዳር መስርቶ ሁለት ልጆች አፍርቶዋል። ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንግዳ አይደለም። በተለያየ የስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ቤተሰቡን ያስተዳድር፣ ልጆቹን ይንከባከብ ነበር። ኮሚዲያን ልመንህ የጤና ችግር ገጠመው። ወደ አገር ቤት እንዲሸኝ ተደረገ። ባለፈው አመት ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ስለኮሜዲያን ልመንህና ጋዜጠኛ ሰሎሞን ሙሉ ታፈሰ ያሉበትን ሁኔታ በማስመልከት የፃፈው ከማሳዘን ባለፈ እንባ ያጭራል። በፒያሳ ጐዳና አንዳንዶች ልመንህን ሲናገሩት የሰማውን ሲገልፅ እጅግ አንገት ያስደፋል። በአንድ ወቅት የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ቀልብ በመግዛት ሳቅ እየጫረ ያዝናና የነበረው ልመንህ በአስከፊና አሳዛኝ ህይወት ውስጥ ይገኛል። በየጐዳናው የምትሳለቁበትና በታወከ ጤናው ላይ ሌላ ቀውስ የምትፈጥሩበት ግለሰቦች እባካችሁ ከዚህ ድርጊታችሁ ተቆጠቡ!?..ሰው የነገ መድረሻውን አያውቅም! እባካችሁ!?…ልመንህ እንዲህ ሆኖ የምታይ “ፍቅረኛ፣ የትዳር አጋርና የልጆች እናት” ምን ይሰማት ይሆን!? ህሊናዋ በሰላም እንቅልፍ ተኝቶ ያድራል?..ፍቅርና ፍቅረኛን በችግሩ ጊዜ አብሮ ካልቆሙለት እንዴት ፍቅር ይባላል?..ግን ልመንህን ፀበል እንኳ የሚወስደው አንድ አርቲስት ይጥፋ?..ልመንህ አለም ፊቷን ያዞረችበት ድንቅና አሳዛኝ ወገን!