ነውረኛ ውሸታም ኣገዛዝ ፡ ወገን በረሃብ አና በድህነት አያለቀ ተኣምር አንፈጥራለን ማለት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በስድስት ወራት ትምህርት ዶክተሬት ያገኘው ኣርከበ አቁባይ በኢኮኖሚ ፖሊሲው ዙሪያ ባለፉት ኣመታት ሲያጭበረብር ቆይቶ ኣልተሳካለትም። የቁጥር ቁልሎችን ከመፍጠር ውጪ ምንም የተገበረው ነገር የለም፤ በላኪዎች የሚገኘውን የውጪ ምንዛሬ በዜሮ ያንደፋደፈ ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገንዘብ በሙስና ያዘረፈ ግለሰብ ዛሬ ላይ ሆኖ ለሚቀጥሉት ኣምስት ኣመታት ተኣምር አንሰራለን በማለት የተለመደ ሃሰቱን አየደሰኮረ ይገኛል፤ተአምር ጠብቁ የሚል ሙድ መያዝ ጀምሯል:: የሃገሪቱ የኢኮኖሚ ኣውታሮች ዲያስፖራው ለቤተሰቡ በሚልከው ዶላር አና የኣለም ነዳጅ ዋጋ በመውረዱ ተደግፎ መኖሩ አየታወቀ በየትኛው መስመር ተኣምር ሊሰራ አንደታሰበ ግራ ያጋባል፤ግራ ከማጋባትም ኣልፉ ግልጽ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ኣገዛዙ ኣጣብቂኝ ውስጥ መሆኑን በገሃድ ያሳያል፥፥በብድር ገንዘብ ተኣምር ሊሰራ ከታሰበ አንዴት ኣበዳሪዎችስ ያበድራሉ፥ወያኔ የተበደረው ገንዘብ ከኣቅም በላይ ከመሆኑ ኣንጻር ካሁን በኋላ ልበደር ማለት ኣሳሳቢ ነው ሲሉ የኣለም ኣበዳሪ ድርጅቶች ሲያማርሩ ተስተውሏል::በባዶ ካዝና ምን አይነት ተአምር እንደሚሰራ አቶ አርከባ ካሳዩን በባዶ ካዝና ተአምር ይሰራ ኢኮኖሚስት ተብለው በአለም አስደናቂ ጉዳዮች መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ::

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሕንጻ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ተዘፍዝፈው መላ ሃገሪቱ በምቾት የተንቆጠቆጠች የመሰላቸው አቶ አርከበ እንደ ዘራፊ ባልንጀሮቻቸው እርሳቸውም በአዲስ ስልት በድህነት እና በረሃብ በተጎዳው ሕዝብ ላይ እየተዘበባቱ ይገኛሉ::ሃምሳ ከመቶ የሚሆነው ገበሬ ምርጥ ነጋዴ ወቶታል የሚለው የሕወሓቱ አህያ አሻንጉሊት ሃይለማርያም ደሳለኝ ገበሬው የማዳበሪያ ኬሚካሎች በፈጠሩት የመሬት ድርቀት የተፈጥሮ ችግሮች በጋረጡበት አደጋ እንዲሁም በአገዛዙ ፖሊሲ ከባድ ችግር ውስጥ መሆኑን ሊናገሩ አልደፈሩም::ያው ተቃዋሚው ስለ ሕዝብ ከመጮህ ይልቅ እርስ በእርሱ በወያኔ አጀንዳ እየተባላ ባለበት በዚህ ወቅት አውሬዎቹ ወያኔዎች በሃገር እና ሕዝብ ሕልውና ላይ እየቀለዱ ይገኛሉ::

ይህ አሳፋሪ እና ጨካኝ አገዛዝ በፖለቲካ ጫና ሕዝቡን እያሰቃየ በብዝበዛ የሃገሪቱን ካዝና አራቁቶ በጉልበት እና በድርድር ፍትህን እየነገደ ተአምር ልሰራ ነው በሚል እጅግ አደገኛ የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን እያራገበ ነው::በመልካም አስተዳደር እጦት ሕዝብ እያለቀሰ ቃልና ተግባር አልገናኝ ብለው ሕዝብን እየተማርረ ራሳቸውን ከሕግ በላይ ያደረጉ ሹማምንት ኢሰብዓዊ ተግባር እየፈጸሙ መብትን መጠየቅም ሆነ ቅሬታ ማቅረብ አሸባሪ እያሰኘ ሃላፊነት በጎደለው ግብረገብነት ባሌለው የሹማምንት እብሪተኝነት የነጻነት መብት እየተደፈጠጠ ዜጎች እየተሸማቀቁ ሐሳብን በነፃነት መግለጽም ሆነ መብትን መጠየቅ ወንጀለኛ አሸባሪ በሚሰኝበት አገር ምን አይነት ተአምር ከሹማምንት ይጠበቃል::ይህችን አይነት ማጭበርበር ለማንም አትበጅም ሃገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ውስጥ ባለችበት በዚህ ሰአት ስልጣን ለሕዝብ ከማስረከብ ውጪ ምንም ተአምር ሊሰራ አይችልም::ባለፉት አመታት የነበሩ የኢኮኖሚ እድገቶች ከቁጥር ቁልል ውጪ ምንም አልፈየዱም::አሁንም ቢሆን በረሃብ የተጎዱ ዜጎቹን መመገብ ያልቻለ ሃሰተኛ አገዛዝ እንዴት አድርጎ ተአምር ሊሰራ ይችላል::የማይመስል ነገር ነው::የወያኔን ተአምር ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ በአንድነት ታግሎ ይህንን ሃሰተኛ አገዛዝ ማስወገድ የለውጥ ሃይሎች ድርሻ መሆን ይገባዋል::በባዶ ካዝና ተአምር እፈጥራለሁ ብሎ መነሳት ራስን ከማጭበርበር ውጪ ምንም ውጤት የለውም::ነውረኛ ውሸታም ኣገዛዝ ፡ ወገን በረሃብ አና በድህነት አያለቀ ተኣምር አንፈጥራለን ማለት በሕዝብ ላይ ማሾፍ ነው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬