ኦነግ፣ ሲነግ፣ ቤነግ፣ ጋሕነግና የኦብነግ ወያኔን ለመጣል አዲስ ጥምረት ፈጠሩ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣የሲዳማ ነፃነት ግንባር፣ የቤንሻንጉል ነፃነት ግንባር፣ የጋምቤላ ህዝብ ነፃነት ግንባርና የኦጋዴን ነፃንት ግንባር ወያኔን ለመጣል አዲስ ጥምረት ፈጠሩ::

Embedded image permalink

Five Ethiopian dissident groups in exile said they have formed an alliance to bring a change of government back home, describing Prime Minister Hailemariam Desalegn’s government as oppressive.

The new group is called the People’s Alliance for Freedom and Democracy, according to a joint statement issued Friday in Oslo, Norway, where the groups met recently.

http://bigstory.ap.org/urn:publicid:ap.org:b49a9121d27a4f6d9c1f00715411b42c

[Wazema Alerts] አምስት በውጪ ሀገር ያሉ ብሄር ተኮር የተቃዋሚ ድርጅቶች አዲስ ጥምረት ፈጥረው በኢትዮዽያ ያለውን መንግስት ለመጣል መዘጋጀታቸውን አስታወቁ። ድርጅቶቹ በኖርዌይ ኦስሎ ባደረጉት የሁለት ቀናት (October 22 & 23) መስራች ጉባዔ በሌሎች ተቃዋሚዎች የሚደረገው ትግል ወደ ውጤት ሊያደርስ ባለመቻሉ ሀገሪቱ ወደተሻለ የፖለቲካ ሽግግር የሚያራምዳት አጀንዳ ቀርፀው ለመንቀሳቀስ ተሰማምተዋል። በሀገሪቱ የሚኖረው የፖለቲካ ለውጥ የሁሉንም ብሄሮች “የራስን ዕድል በራስ የመወሰን” መብት የሚያከብርና የአንድን ቡድን የበላይነት እንዲያበቃ የማድረግ ተልዕኮ ይኖረዋል። ጥምረቱን የመሰረቱት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣የሲዳማ ነፃነት ግንባር፣ የቤንሻንጉል ነፃነት ግንባር፣ የጋምቤላ ህዝብ ነፃነት ግንባርና የኦጋዴን ነፃንት ግንባር ናቸው። ድርጅቶቹ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ባወጡት መግለጫ የአዲሱ ጥምረት መጠሪያ Peoples Alliance for Freedom and Democracy (PAFD)ይሆናል። እነዚህ ድርጅቶች ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ስም በኤርትራ ከሚንቀሳቀሱት ጋር የተዛመዱ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ማረገገጥ አልቻልንም። በኤርትራ የሚንቀሳቀሰው አርበኞች ግንቦት ሰባት በቅርቡ ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄና ሌሎች ድርጅቶች ጋር ጥምረት መፍጠሩን አስታውቆ ነበር።