ድርቁ የትምህርት ሂደት እያስተጓጐለ ነው። የእንደርታ ወረዳ ተማሪዎች ትምህርታቸው እያቋረጡ ናቸው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ድርቁ የትምህርት ሂደት እያስተጓጐለ ነው። የእንደርታ ወረዳ ተማሪዎች ትምህርታቸው እያቋረጡ ናቸው።
በእንደርታ ወረዳ የሚገኙ የ9 10 11ተማሪዎች በድርቁ ምክንያት ትምህርታቸው እያቋረጡ ይገኛሉ። ተማሪዎቹ
፩) ከገዳግዲ ትምህርት ቤት =20
፪) መረበይቲ “”=13
፫) ኣራጉረ “”=5
፬) ማይመኽደን “”=25 እና ሌሎች በርካታ ተማሪዎች የመልቀቅያ ወረቀት እንዲሰጣቸል ማመልከቻ ኣስገብተዋል።
እነዚ የተወሰኑ ተማሪዎች በድርቁ ምክንያት መደበኛ ትምህርታቸው መቀጠል ያልቻሉት ቀንቀን ስራ እየሰራን ማታማታ መማር ስለፈለግን መልቀቅያችን ስጡን የሚል ጥያቄ ለትምህርት ቤቶቻቸው ኣቅርበዋል።
የእንደርታ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሓላፊዎች ለማንኛውም ተማሪ የመልቀቅያ ወረቀት እንዳይሰጥ፣ ማንኛውም ወላጅ ልጁ ትምህርት ያቋረጠ ካለ እርዳታ እንደማይሰጠው የሚከለክል መመርያ ኣውጥተዋል።
ሓላፊዎቹ የትምህርት መልቀቅያ ወረቀት መስጠት የሚቻለው ቤተሰቡ ከቀበሌው ሙሉ በሙሉ ለቀው እሚኸዱ ከሆኑ ብቻ ነው የሚል መመርያ ኣስነግረዋል።
ተማሪዎቹ ድርቁ መቋቋም ስላልቻሉ “ኣንሄድም” እያሉ እያቋረጡ ይገኛሉ።
ኣቶ ኣባይ ወልዱ በኣፅቢና ክልተ ኣውላዕሎ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት ከህዝቡ ” ልጆቻችን በድርቁ ክብደት ትምህርት ቤት ኣንሄድም ብለውናል” ብለው ገልፀውላቸው ነበር።
ድርቅ ያጠቃቸው ወረዳዎች ልጁ ትምህርት ያቋረጠበት ወላጅ እርዳታ እንደማይሰጠው መመርያ ወርዶባቸዋል።
ሰሞኑን በመቐለ ፣ ውቕሮና ሌሎች የትግራይ ከተሞች ከ10 ሺ በላይ ካድረ በከፍተኛ ኣበል የተከፈላቸው ሲሆን እምበር ተጋዳላይ እየተዘፈነ ለመግለፅ የሚከብድ ብር እየባከነ ይገኛል።
ህወሓት ባንድ እጇ ለፈረንጆች እየለመነች በሌላኛው እጇ በሚልዮን የሚቆጠር ትመዘብራለች።
ነፃነታችን በእጃችን ነው………!
IT IS SO……!
Amdom Gebreslasie