በሃገራችን የተከሰተው ድርቅ በአለም መገናኛ ብዙሃን የቀን ተቀን አጀንዳ ሆኗል:: (2015 Drought in Ethiopia)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
– “ሁኔታው አስጊ ነው>::” – ጆን አይሊፍን UN/FAO =
– “የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎቱ በሶርያ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከፈጠረው ፍላጎት ሊልቅ ይችላል::” አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ =
– “ችግሩ ከሀገሪቱ አቅም በላይ አይሆንም፣ ከቁጥጥር የወጣ አይደለም” የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት =
– “ድርቁ ያስከተለውን የምግብ እጥረት ለመቋቋም ኢትዮጵያ አለማቀፉን ማህበረሰብ 596 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ጠይቃለች::” ኒውዮርክ ታይምስ =
– “መንግስት የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የያዘው መንገድ ለችግሩ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በቂ አይደለም::” አቶ ቆስጠንጢኖስ በርሄ =
– “ኤሊኒኖ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ቢከሰትም ጉዳቱ ኢትዮጵያ ላይ በርትቷል፡፡” ሮይተርስ =
የወያኔ ባለስልጣናት ድርቁ ያስከተለው ችግር ከቁጥጥር አልወጣም ቢሉም አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን እና ድርጅቶች ግን ድርቁ እጅግ አስጊ መሆኑን እን በሚቀጥለው ሶስት ወር ብቻ የተጎጂው ቁጥሮች ወደ አስረአምስት ሚሊዮን እንደሚያድግ በመናገር ላይ ይገኛሉ::አለማቀፉን ለጋሾች ወደ 600 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ እርዳታ እየለመነ እየተማጸነ በሌላ ጎን “ችግሩ ከሀገሪቱ አቅም በላይ አይሆንም፣ ከቁጥጥር የወጣ አይደለም” የሚለው ወያኔ ለፖለቲካው አጀንዳ ማስፈጸሚያ እያዋለው መሆኑ ሲታወቅ “መንግስት የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የያዘው መንገድ ለችግሩ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በቂ አይደለም::” የሚል ትችት ከራሱ ምሁራኖቼ ከሚላቸው ደየደረሰበት ነው::
የኤሊኖ ክስተትን ተከትሎ በአገሪቱ የተፈጠረው ድርቅ ከ10-15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ለምግብ እጥረት ሊያጋልጥ እንደሚችል ኦክስፋምና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰሞኑን ባወጡት ሪፖርት የገለፁ ሲሆን ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገራት በበለጠ ክፉኛ እንደጐዳት ያመለከተው ኒውዮርክ ታይምስ፤ ድርቁ ያስከተለውን የምግብ እጥረት ለመቋቋም መንግስት አለማቀፉን ማህበረሰብ 596 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ የጠየቀ ቢሆንም በሶርያና በኢራቅ ያለው ጦርነት ብዙ ድጋፍና እርዳታ በመፈለጉ የኢትዮጵያ ጥያቄ ትኩረት አለማግኘቱን ጠግቧል፡፡ መንግስት እስካሁን 192 ሚሊዮን ዶላር ከካዝናው አውጥቶ ለድርቁ መመደቡን የጠቀሰው ዘገባው፤ ይሄ ግን ከሚያስፈልገው የምግብ እርዳታ አንፃር በቂ ስላልሆነ አለማቀፉ ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብሏል፡፡
የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በበኩሉ፤ የተባበሩት መንግስታት 15 ሚሊዮን ህዝብ እርዳታ ፈላጊ ሊሆን ይችላል በሚል ያወጣውን ሪፖርት በመጥቀስ፣ የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎቱ በሶርያ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከፈጠረው ፍላጎትም ሊልቅ እንደሚችል አመልክቷል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተጠሪ ጆን አይሊፍን፤ “ሁኔታው አስጊ ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ የዘገበው ሮይተርስ በበኩሉ፤ አለማቀፉ ህብረተሰብ ትኩረቱን ወደ ኢትዮጵያ በማድረግ እርዳታ መስጠት እንዳለበት አሳስቧል፡፡
በኢትዮጵያ የዩኤስኤድ ዳይሬክተር ዴኒስ ዌለር ለሮይተርስ እንደገለፁት፤ የምግብ እርዳታውን ለጋሾች በተገቢው መጠን እንዳያቀርቡ በደቡብ ሱዳን ያለው የእርስ በእርስ ግጭት እንቅፋት ሆኗል፡፡ ከጦርነቱ ሽሽት ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ስደተኞችን መመገብ የአለማቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የወቅቱ ትኩረት መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡እንዲያም ሆኖ በተለይ ለህፃናት የተመጣጠነ ምግብ ለማቅረብ ዩኤስኤድ ጥረት እያደረገ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ የኤሊኒኖ ክስተቱ ከ60 ዓመት በኋላ የተከሰተ ጠንካራው የአየር መዛባት መሆኑን የጠቆመው ሮይተርስ፤ ኤሊኒኖ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ቢከሰትም ጉዳቱ ኢትዮጵያ ላይ በርትቷል ብሏል፡፡
የመረጃ ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ #ምንሊክሳልሳዊ