የእውነት ቡሉኮ : የባንዲራችን ጉዳይ የዘር ፖለቲካ እና የማህበራዊ ድህረገጽ የአጀንዳ ጡዘት
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi – የሳምንቱን መጨረሻ እረፍት አቋርጦ መጻፍ ቢከብድም እውነትን እየጣሉ የማያነሱ የፈጠራ ታሪክ ዲስኩረኞች በማይረቡ ቃላቶቻቸው መሬት ላይ ካለው ሃቅ ወጥተው የማህበራዊ ድህረገጽን በዘረኝነት አጀንዳ የሚያጥወለውሉ የሃገርን ጉዳይ በጎጥ ፖለቲካቸው የሕዝብን የነጻነት ጥያቄ በፈጠራ ታሪኮች ለመበረዝ የሚሮጡ ቅጥረኞች አጀንዳ ፈጥረው እና አስፈጥረው የዋሃንን በስሜት የሚያጦዙ የአምባገነኖችን የስልጣን እድሜ በርግብግቢት ትንፋሻቸው ለመጨመር ተበርዘው እና ተከልሰው የተላኩ ባልተሰላ ፖለቲካ ያልበሰሉትን የሚያጦዙ መሬት ላይ ያለውን ሓቅ ወደ ሃስት ቀይረው በማህበራዊ ድህረገጽ የሚያሽካልሉ ባንዲራችንንም ሆነ ሕዝባችንን ሊከፋፍሉት ይሁን ሊያደናግሩት ከቶ አይቻላቸውም::
በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ትልቅ የፍቅር እና የአንድነት ትሥሥር አለ::ይህን የትሥሥር ገመድ ማንም ሊበጥስ አይቻለውም::ሞክረውም ያልተሳካላቸው ዛሬም እየለፉ እየከሰሙ ስልታቸውን እየቀያየሩ ቢንጠራሩ የሚፈልጉትን ለማድረግ አልተሳካላቸውም::የኢትዮጵያ ባንድራ የማይበረዝ የማይከለስ አረንጓዷ ቢጫ ቀይ ነው:ለመቀየርም ይሁን ለማፋለስ መሞከር አይደለም እድሉም የላቸውም የሃይለስላሴ አርማ የነበረው የይሁዳ አንበሳ ቀጥሎም የደርግ ኢሕድሪ አርማ ዛሬም የወያኔ ማስጠሎ ኮከብ በባንዲችን ላይ በመፈራረቅ ተወታትፈዋል::ከንጉሱ እና ከደርግ ወያኔን ለየት የሚያደርገው በጉልበት መሃል ላይ የሰነቀርኩትን ኮከብ ውደዱልኝ ብሎ ድርቅ ከማለት ዘሎ ሕግ ማውጣቱ ነው:;አስከፊ የተባሉት ያለፉት ስርኣቶች እንኳን ባንድራ መሃል የሰነቀሩትን አርማ ውደዱ ሊሉ አይደለም ታሪካዊ ባንዲራ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ እንደሆነ ሲያስተምሩ አልፈዋል::የመህል ላይ ኮከቡ ይሁን የክልል ባንድራዎች የተባሉትም በጎሳ ፌዴራሊዝም ላይ ተመስርተው የተቀለሙ ስልሆኑ ተቀባይነታቸው ወያኔ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ብቻ ነው::
ወደ ዘር ፖለቲካ ስንመጣ የወያኔ የዘረኝነት ፖሊሲው በሁሉ አካሎች በሃገር ቤት እና በውጪው ሃገር ይራመዳል::በሃገር ቤት ለሕወሓት ተገዢ በሆኑ ጥቅመኛ ካድሬዎች ሲሆን በውጪው ሃገር ደግሞ ለዚሁ የዘር ፖለቲካ ተመልምለው ሰልጥነው የተሰማሩ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች እና አጀንዳ ፈጣሪዎች አዛኝ መሳዮች አስመሳይ ፖለቲከኞች አጉል የፖለቲካ ተንታኝ መስለው በመቅረብ በማደናበር የማህበራዊ ድህረገጽ መወዛገብን የሚፈጥሩ የወያኔ የከፋፋይ ፖሊሲ አሸርጋጅ ዲያስፖራዎች ስራው ይሰራል::ከሕወሓት ከኦሕዴድ እና ከብኣዴን የተወጣጡ ቡድኖች የጎጥ ርእዮት አለማቸውን ይዘው የዘረኝነት መርዝ በመርጨት ላይ ይገኛሉ::ኢትዮጵያዊነትን ከጅምሩ በሕወሓት እንደታሰበው ነቅሎ ለማጥፋት ለመበረዝ እና የጋራ ማንነት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ሕዝቡ ከኢትዮጵያዊነቱ ይልቅ ዘሩ ላይ እንዲያተኩር ከፍተኛ የመከፋፈል ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ይገኛሉ::በመሬት ላይ የሚገኘው ሕዝብ በቂ ንቃተ ሕሊና ስላለው በተለያዩ አከባቢዎች በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በካድሬዎች እንደሚፈጸሙ በተለያየ ጊዜ አጋልጧል::በማህበራዊ ድህረገጽ የሚሰበከው ዘረኝነት በወያኔ መዳፍ አልጨበጥ ያለውን ዲያስፖራ ለመከፋፈል የተሸረበ ሴራ ነው::በተለያዩ የኢትይኦጵያ ብሄሮች ስም እየተነገደ የዋሃንን በማታለል ዲያስፖራውን በማህበራዊ ድህረገጽ በሚደረግ ከፋይ አጀንዳ ለማለያየት እና ለማበሳጨት የሚደረጉ እኩይ ተግባራትን በጋር ልንዋጋ ይገባል::#ምንሊክሳልሳዊ