በድርቅ የተጠቁ የዓረና ኣባላት በትግራይ የእርዳታ እህል ድርጅታቹ ይስጣቹ ተብለው ተለይተዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
” የመጣው እርዳታ ጥቂት ነው … !”
~*~*~*~*~*~*~*~*~
(የቀበሌ ኣመራሮች)
በድርቅ የተጠቁ የትግራይ ቀበሌዎች ኣመራሮችና ካድሬዎች ህዝቡን እየሰበሰቡ ” ለቀበሌያችን የተመደበ የእርዳታ እህል በጣም ጥቂትና ለሁሉም ህዝብ ሊዳረስ ስለማይችል በጣም ድሃ ለሆኑና የሚሸጥ የሚለወጥ ለሌላቸው ሰዎች ብቻ ነው የሚሰጠው።
………… በዚህ መሰረትም እርስ በራሳቹ እየተጠቋቆማችሁ በጣም ለከፋው ሱው እንዲ ደርሰው ኣድርጉ ” የሚል ትእዛዝ ኣውርደዋል።
ህዝቡ ግን ” ዝናቡ ማሳ ለይቶ ኣልዘነበም። በዛላይ ከብቶችም በድርቅ ስለተጠቁ ተሽጠው የሚያወጡት ዋጋ እዚ ግባ ሊባል የሚችል ኣይደለም። ስለዚ እኛ እገሌ ከእገሌ ይሻላል የምንልበት ኣሳማኝ ምክንያት የለንም።
የእገሌ ልጆች ይብሉ የእገሌ ልጆች ይሙቱ ብለን ኣንፈርድም ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ሓጥያት ሰርተን ልንፀፀት ኣንፈልግም ” በማለት ኣቋሙ እየገለፀ ነው።
ስራው እንዲተገብሩ ትእዛዝ የተቀበሉ የቀበሌ ኣመራሮችም ” ይህ ትንሽ እርዳታ ካላብቃቃን እርዳታ የሚባል እንደማይሰጠን ትእዛዝ መጥቶናል። በግልፅ መጠቆም የማትደፍሩ ከሆናቹ በየግል መስርያ ቤት እየመጣቹ ጥቆማቹ ልትሰጡን ትችላላቹ ” በማለት መልእክታቸው እየገለፁ ናቸው።
ኣብዛኛዎቹ ቀበሌዎቹ ይህ “ኣነ ገድድ”( እኔ ብስ) ብለው ከሌላ ሰው ቀምተው እርዳታ ለመቀበል ዝግጁዎች ሊሆኑ ኣልቻሉም። በዚህ ኣቋማቸው ህዝቡ ኣጣልቶና ከፋፍሎ ለመግዛት የተሴረ ተንኮል ኣክሽፈዋል።
የቀበሌ ኣመራሮች የወረደባቸው ኣስገዳጅ መመርያ ለመፈፀም እየተጠቀሙበት ያሉት ዘዴ ደግሞ ጎረቤታሞች የኣንዱ ቤተሰብ የሚያውቀው መረጃ ኣሳልፎ እንዲነግራቸው ካደረጉ በኋላ ዘወር ብለው ቀጥሎ ወዳለውቤት በመሄድ ስለ መጀመርያ የጠየቁት ቤት መረጃ እንዲሰጥ ያደርጉታል።
ስለሁሉም ቤቶች የሚጠየቁት ጥያቄዎች
* ” ጎረቤትህ ኣምና ስንት ኩንታል እህል ኣምርቷል፣
*ኣሁን በቤቱ ስንት ኩንታል እህል ተከማችቶ ይገኛል፣
* ቤተሰቡ የሚረዳው የቅርብ ሰው ኣለወይ ” ተብለው እራስ በራሱ እንዲሳለል እያደረጉ ናቸው።
ከዚህ ምደባ ውጭ የሆኑ ሰዎች ኣስቀድመው ታውቀው ከውድድር ውጭ ተደርገው ተለይተዋል።
እነዚህም
1) የዓረና ኣባላት…ድርጅታቹ ይስጣቹ ተብለው።
2) ከኣንድ በላይ ከብት ያላቸው…ሽጣቹ ብሉ ተብለው
3) የመንግስት ሰራተኛ ልጅ ያላቸው…ልጃቹ ይርዳቹ
4) የመዳበርያ፣ ደደቢት፣ ምርጥ ዘር እዳ መክፈል
ያልቻሉ።
5) የተወሰነ ቡቃያ ያበቀለ ገለባ ይገኝበታል ከተባለ
8
6) ከቀበሌ ኣመራሮችና የተጣሉና… “ዓንቃፊ”(የመንግስት እቅዶች ኣደናቃፊ ነው) የተባለና በተቃዋሚነት የተፈረጁ ሰዎች ናቸው።
መጥተዋል እየተባለ ያለው የእርዳታው እህል በድርቅ ክፉኛ ተጠቅተዋል የተባሉ 190 ቀበሌዎች ብቻ የሚከፋፈል ነው።
እነዚህ 190 ቀበሌዎች በድርቁ ኣደጋ በጣም የተጠቁ የተባሉ ናቸው እንጂ በኣደጋው በጣም ብዙ ቀበሌዎች ተጠቅተዋል።
ኣቶ ኣበይ ወልዱ ” በተወሰኑ(190) ቀበሌዎች ኑዋሪ የሆነ ከ900 ሺ ህዝብ በላይ ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል” ብለው እንደገለፁት የሚታወቅ ነው።
ለኣንድ ሚልዮን(በኣገራችን በድርቅ ከተጠቃ ህዝብ ትግራይ 11.% የሚሸፍን) የሚጠጋ ህዝብ 200 ሚልዮን ብር ( ከሚያስፈልገው እርዳታ 2.5% ) ብቻ በመመደባቸው ምክንያት ያጋጠመ እጥረት የፈጠረው ችግር ህዝባችን “እኔ ብስ እኔብስ” ብሎ ተጣልቶ እርዳታ እንዲቀበል እያስገደዱት ነው።
የሄ ጀግና ህዝብ ደርግ ለመደምሰስ ሂወቱ ለመሰዋት ” እኔ ብስ እኔ ብስ ” ብሎ እንዳልተሰዋ ኣሁን ለቁራሽ እንጀራ ተካክዶና ተጣልቶ እንዲቀበል ተንኮል ምሰው እያጫረሱት ነው።
ይሄ የካድሬዎች “… የመጣው እርዳታ በቂ ስላልሆነ…”
የሚለው መመርያ ኣንድ ትልቅ ሃቅ ያጋለጠ፣ ገሃድ ያደረገና ፍንትው ኣድርጎ ያመላከተ ነው።
ለህወሓት መራር እሬት የሆነው የድርቁ ስፋት ከሚነገረው በእጅጉ የላቀ፣ ድርቁ ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቅድመ ዝግጅት ያልተደረገበት መሆኑና ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ እየሆነ እንዳለ የሚያሳይ ነው።
በእንቅርት ላይ ጀሮ ደገፍ እንደሚባለው የመጣው እህል በ77 ዓ/ም ማ.ሌ.ሊ.ት እንዳጭበረበረችው ኣሁንም “መጋዘን ሞላ፣ ለኣባይ ግድብ መስርያ” ወዘተ በሚል ምክንያት ለዝርፍያ ተጋልጦ ይገኛል።
ህወሓት በትግራይ ኣጋጥሞ ያለው ኣደገኛና ሰፊ ቦታ የሸፈነ ድርቅ ያለበት ሁኔታ በግልፅ ለመግለፅ ኣልፈለገችም ኣልያም ስፋቱ ለማወቅ ኣቅም የላትም ማለት ነውና ሓቁ ለህዝቡ ይፋ እንድታደርግ እንጠይቃለን።
የድርቁ ኣደጋ በዓፋር ክልልም ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ከመሆኑ በተጨማሪ ታጣቂዎች መኪና እያስቆሙ ከተሳፋሪዎችና ከሽፌሮች ብር እየተቀበሉ መሆኑ ታውቋል።
በኣማራ ክልል ዋግኽምራ ዞንም የድርቁ ሁኔታ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ የታወቀ ሲሆን ኑዋሪዎቹም ወደ መቐለ ከተማ መሰደድ ጀምረዋል።
እባካቹ በህዝቡ ረሃብና ችግር ሳትጨነቁ የድርጅታቹ መጥፎ ስራ ለመደበቅና ሊጠፋ ይችላል ብላቹ የምትፈሩት ስሟ ለመከላከል ለምትደክሙና ሆዳቹ ሊቆርጣቹ ኣይገባምና ፊታቹ ወደ ተራበ ህዝባቹ እንድትመልሱ እላለው።
ከሰው ረሃብ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚፈልግ ሰውም ፓርቲም የለምና ይሄ ፅሁፍ በሰብኣዊ ርህራሄና ሂወት ለማዳን የሚደረግ ጥረት ኣካል ኣድርጋቹ እንድትወስዱት ኣሳስባለው።
ነፃነታችን በእጃችን ነው…………!