ወደ ቢጫነት የተቀየረ ጥርስን ማከሚያ መንገዶች
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ወደ ቢጫነት የተቀየረ ጥርስን ማከሚያ መንገዶች :-ስለ ውበት ሲታሰብና ያማረ ገጽታን ለመላበስ ሁሉም የሰውነት ክፍሎች በተመጣጠነ መልኩ አይነ ግቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
አምሮና ደምቆ መታየት ሲታሰብ ደግሞ የፊት ገጽታ በተለይም ያማረና እና ማራኪ ፈገግታ ቀዳሚው ነው፤ ላማረ ፈገግታ ደግሞ ጤንነቱ የተጠበቀ እና ንጹህ ጥርስ ወሳኝ ነው።ታዲያ ይህ የውበት መገለጫ የሆነው ጥርስ ደህንነቱ ካልተጠበቀ እና እንክብካቤ ከጎደለው ያለ ጊዜው ያረጀ እና የተበላሸ ሆኖ ከውበት መገለጫነቱ ይልቅ የጤና ጠንቅነቱ ያመዝናል።ጥርስ በእድሜ፣ ከእንክብካቤ ማነስ፣ እንደ ሻይ፣ ቡና እና ሲጋራ ያሉ ለጥርስ መበላሸት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን አብዝቶ ከመጠቀም እና አልፎ አልፎ በዘር ከሚመጡ ችግሮች መነሻ የነበረውን ጥንካሬና ቀለም ሊያጣ ይችላል።
ባክቴሪያ መከላከያ መድሃኒቶችን አብዝቶ መጠቀም፣ የአየር ሁኔታ፣ ኢንፌክሽንና መሰል ምክንያቶችም ጥርስ የነበረውን ቀለም እንዲያጣ መንስኤዎች ናቸው።ታዲያ ይህን አይነት ችግር ጥርስዎ ላይ ሲከሰት ወደ ህክምና ተቋም መሄድና ያንን ለመመለስ የሚያደርጉት የህክምና ክትትል በጣም ውድ እና ውጤቱም የታሰበውን ያህል እንዳልሆነ ይነገራል።ከዛ ይልቅ ግን ይህን ችግር ለመከላከል እና ወደ ቢጫነት ወይም የወየበ እና የበለዘ ጥርስን ቀለም ወደ ነበረበት ለመመለስ በቤት ውስጥ በሚዘጋጁ ማከሚያ መንገዶች መጠቀም ይቻላል።
ለዚህም ደግሞ፦
ቤኪንግ ሶዳ፦ ሩብ የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ ከተመጣጣኝ የጥርስ ሳሙና ጋር በመቀላቀል ጥርስን መቦረሽና በቀዝቃዛ ውሃ በአግባቡ መለቃለቅ፥ ይህንንም በሳምንት ለሁለት ጊዜ ያህል መጠቀም።
ወይም ይህን ውህድ በአንድ የሻይ ማንኪያ የሎሚ ውሃ ቀላቅሎ ጥርስን መቦረሽና በቀዛቃዛ ውሃ መታጠብ እና መለቃለቅ፤ መጠኑ የበዛ ቤኪንግ ሶዳ መጠቀም የጥርስ መስታውትን ስለሚጎዳ በአግባቡ መሆን ይኖርበታል።
የብርቱካን ልጣጭ፦ ትኩስ /ከተላጠ ደቂቃዎች ያላለፉት/ የብርቱካን ልጣጭም ወደ ቢጫነት የተቀየረ ጥርስን ለማከም ይረዳል። ይህን ማታ ማታ ከመኝታ በፊት በተጎዳው ጥርስ ላይ አድርጎ ማሸት።
በልጣጩ ላይ ያለው ቪታሚን ሲ እና የካልሺየም ውህድም ጥርሱ ላይ የደረሰውን አደጋ የመከላከል እና በጊዜ ሂደት የማስወገድ አቅም አለውና ትኩስ የብርቱካን ልጣጭን ተጠቅመው የተጎዳ ጥርስዎን ያክሙበት።
ይህን ሙከራም ማታ ማታ ለተወሰኑ ሳምንታት በማድረግ ቢጫውን ጥርስዎን ማከም።
እንጆሪ፦ የእንጆሪ ፍሬም ቢጫን ጥርስ ወደ ቀድሞ ማንነቱ ለመመለስ የሚረዳ የፍራፍሬ አይነት ነው። ይህን ፍራፍሬ በጥቂቱ ቆራርጦ በተጎዳ ጥርስ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማቆየት።
አልያም ደግሞ አንድ የእንጆሪ ፍሬን ከቤኪንግ ሶዳ ጋር በመቀላቀልና በማዋሃድ በተጎዱ ጥርሶች ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማቆየት እና ጥርስን በአግባቡ ቦርሾ በንጹህ ውሃ መለቃለቅ።
ይህንን በቀን ሁለት ጊዜ ጠዋትና ማታ ከአራት ሳምንት ላልበለጠ ጊዜ በመተግበር ጤናማ ጥርስዎን ማግኘት ይችላሉ።
ሎሚ፦ ወደ ቢጫነት ለተቀየረ እና ለወየበ ጥርስ ሌላው መፍትሄ ደግሞ ሎሚን መጠቀም ነው።
በትንሽ የሻይ ማንኪያ የተዘጋጀ ጨው እና እስከ አራት ጠብታ የሎሚ ውሃን በመቀላቀል ውህዱን ጥርስ እና ድድ ላይ ለደቂቃዎች ማቆየት።
ቀጥሎም አፍን ሳይጉመጠመጡ ጥርስዎን በአግባቡ ቦርሾ በውሃ መለቃለቅ።
ይህን ደግሞ በቀን ሁለት ጊዜ ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት መጠቀም እና ጥርስዎን ማከም።
የገበታ ጨው፣ ለምግብ ማጣፈጫነት የሚጠቀሙት ጨው በአስገራሚ ሁኔታ የተበላሹና ማንነታቸውን ያጡ ጥርሶችን የማከምና እንዲያገግሙ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ነው።
በጥርስ ቡርሽዎ ላይ ከጥርስ ሳሙና ይልቅ ደቃቅ ጨውን በማድረግ ጥርስዎን ጠዋት ከቁርስ በፊት መቦረሽ።
ወይም ደግሞ ንጹህ እና አነስተኛ መጠን ያለውን ከሰል ከዚህ ጨው ጋር ቀላቅሎ ጥርስን መቦረሽ።
አልያም ጨውን ከቤኪንግ ሶዳ ጋር በመቀላቀል ጥርስን በጥንቃቄ መቦረሽ፤ ይህን ሲያደርጉ ግን መጠኑ እጅግ አነስተኛ እና በተባለው ልክ መሆን ይገባዋል።
በትንሽ የሻይ ማንኪያ ሩብ ቤኪንግ ሶዳን ከግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው ጋር መቀላቀል እና ጠዋት ጠዋት ብቻ ለሁለት ሳምንታት መጠቀም ይኖርብወታል።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የቤት ውስጥ ህክምናዎች ቀላል ወጭ እና ጊዜ የሚጠይቁ በመሆናቸው፥ ወደ ቢጫነት ተቀይሮ የተበላሸ ጥርስዎን በአግባቡ ያክሙባቸው።
ምንጭ፦ top10homeremedies.com