የስርኣቱ ሰዎች ፍትህን በወሲብ እና በጎሳ እየቸረቸሩት መሆኑን ሰማን አዘንን!!! ግን እስከመቼ?? (ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኢትዮጵያችን የፖለቲካ ስልጣን ፍትህን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ባላንጣን እና ንጹሃንን ለማጥቃት መጠቀም በወያኔ ጉጅሌ ባለስልጣናት የተለመደ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ የሆነው የስርኣቱ ሰዎች ፍትህን በወሲብ ድርድር እና በጎሳ እየቸረቸሩት መሆኑን ሰማን አዘንን!!!ግን እስከመቼ?? ተቆጣጣሪ የሌላቸው ለፖለቲካው ተገሺ የሆኑት የፍትህ አካላት ለከፍተኛ የሙስና አደጋ እና ልክስክስ ባህሪያት መጋለጣቸው የስርኣቱ መሪዎች የፈጠሩት መሆኑ አይካድም::

የአንድ አገር ፍትህ የሚኮላሸው የፖለቲካ አስተዳደሩ የፖሊስ ውጤት ሲሆን በሃገራችንም የተሰጣቸውን የሙያ ሥነ ምግባር ዘንግተው ዳኝነትና ፍትሕን በአገር ልጅነት ወይም በብሔር ግንኙነት የሚሸጡና ለወሲብ ድርድር የሚያቀርቡ መስፋፋታቸው እየሰማን እያየን ነው ጥናቶችም እየመሰከሩባቸው ነው::ካሁን በፊት በኢትዮጵያ በኪነጥበቡ ዘርፍ ያለው ኪነጥበብን ለወሲብ መሸቀጫነት መዋሉ እንዲሁም በተለያዩ ቢሮዎች የስራ ጉዳዮች ለወሲብ ሸቀጥነት ለድርድር መገልገል ከአስፈጻሚዎች ስነምግባር ጎዶሎነት መሆኑ ታዝበት ካቀረቀርንበት ቀና ሳንል ፍትህን የሚያል ትልቁ የሰው ልጆች የሰባዊ መብት ክፍል ለአገር ልጅነት መጠቃቀሚያ ለጎሳ ፖለቲካ ማስፈጸሚያ እና ለወሲብ ድርድር መቅረቡ እጅግ ከማሳፈሩም በላይ የስርኣቱን ወራዳነት ያሳያል::

ሙስና በተንሰራፋበት በፍትሕ መድረክ ላይ ዜጐች በእኩልነት አይስተናገዱም፡፡ የዜጎችን መብት ይሁን ሙስናን የመታገያው የመጨረሻው መተማመኛ ተቋም የፍትሕ ሥርዓቱ በሙስና ስለተፍረከረከ ባኢትዮጵያ ሕግ እንዳሌለ በተደጋጋሚ እያየነው ነው::ሰዎች ካለወንጀላቸው ይታሰራሉ::በንጻ ተለቀ ደግመው ይታሰራሉ ከዚያም ሲያልፍ ከፍተኛ ድብደባ እና ግርፋት ይደርስባቸዋል::ይህ ማለት ብዙ ሳንሄድ የሚያሳየን ፍትህ አለመኖሩን ነው::ፍትህ ካሌለ ደሞ መንግስት የለም ማለት ነው::ግን እስከመቼ በዚህ ሁኔታ እንቀጥላለን? ነጻና ገለልተኛ ያልሆነ ፍርድ ቤት አለመኖር ስልጣንን አላግባብ መጠቀም ማለት ተቆጣጣሪ መንግስታዊ አካል እስካሌለ ድረስ መግስት የለም ማለት ነው::መንግስት ባለበት አገር በጎሳ ላይ በጎጥ ላይ የተመሰረተ ፍትህ እንዲሁም ወሲብን ለድርድር ያቀረበ ፍትህ ከዚያም ላቅ ሲል የፖለቲካ ፍጆታ ፍርድ ቤቶችን ማድረግ እጅግ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው::ፍትህ ይሰው ልጆች መብት እንጂ የጥቂቶች የፖለቲካ መነገጃ የስልጣን መባለጊያ እና የግል መገልገያ ሸቀጥ አይደለም:: – ግን እስከመቼ??