የዞን ዘጠኙ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በዋስ ተፈታ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
#Ethiopia #Freezone9bloggers የወያኔው ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ካልወንጀላቸው ካሰራቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ውስጥ በማጎሪያው ካምፕ አስሮት የነበረውን ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በ20.000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ወስኗል::ግፊት እና ጫና መቋቛም ያቃተው የወያኔው ስርኣት በርካታ ንጹሃንን አሁንም በየማጎሪያ ካምፕ አስሮ ይገኛል:: ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ የሚቀጥልወ ቀጠሮው የመከላከያ ማስረጃ ለመስማት ለህዳር 27/2008 ቀጠሮ የተሰጠ ሲሆን ከሃገር እንዳይወጣ በወያኔ ማእቀብ ተጥሎበታል:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
