ብሔራዊ ጭቆናን አንቀበልም! መብቶቻችን ተሟልተው እስኪከበሩ ሕዝባዊ ትግላችን ይቀጥላል! (ድምፃችን ይሰማ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ብሔራዊ ጭቆናን አንቀበልም! መብቶቻችን ተሟልተው እስኪከበሩ ሕዝባዊ ትግላችን ይቀጥላል! ድምፃችን ይሰማ
#‎EthioMuslims‬ ‪#‎EthioMuslimPeacefulStruggle‬ ‪#‎Fidake‬
Voice Aau Muslims's photo.
 ማክሰኞ ጥቅምት 9/2008
የኢትዮጵያ ሙስሊም ብዙ የሀይማኖት መብት ጥያቄዎች ቢኖሩትም የትግላችን መነሻዎች ግን ሶስት ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ ሆኖም ቀደም ሲሉ የነበሩት በሀይማኖታችን ላይ የሚደርሱ ትንኮሳዎች የመንግስት ፖሊሲ hoነው በመቀጠላቸው ትግላችን በሶስት ጥያቄ ከመታጠር ወጥቶ በእምነታችን እየደረሰብን ያለውን ብሄራዊ ጭቆና ወደ ማስወገድ ፊቱን አዙሯል፡፡ ይህ ሂደት የህዝብን አቅምና ተጨባጩን ሁኔታ ያገናዘበ፣ መስዋእትነቶችም ከጥቃቅን ቀዳዳዎች ይልቅ ትልልቅ ችግሮቻችንን በሚፈቱበት ተገቢ ቦታ እንዲውሉ የሚያደርግ ማዕቀፍን የያዘ ሆኖ በህዝባዊ ተሳትፎ ቢቀጥልም በመንግስት እየተተገበረ ያለው ብሄራዊ ጭቆና ግን ከእለት ወደ እለት አስገራሚ ገፅታ እየተላበሰ ይገኛል፡፡
በብስለት የበለጣቸውን ህዝብ በመተናኮስ ወደሁከት ለመውሰድ ዘወትር ሴራ የሚሸርቡት የመንግስት ሐይላት እንኳን ህዝብን ከሚመራ የተደራጀ አካል ቀርቶ ጤነኛ አዕምሮ ካለው ግለሰብ የማይጠበቅ ትንኮሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በኢድ አል አድሀ እለት ‹‹ፊዳከ›› የሚል ቲሸርት ለብሰው ለስግደት አደባባይ የወጡ ሙስሊሞችን በማሰር ከእምነትም አልፎ ‹‹የመረጥኩላችሁን ነው የምትለብሱት›› የሚል የትዕቢት መልዕክት ያስተላለፈልን መንግስት ዛሬ ደግሞ በትምህርት ተቋማት ሳይበቃ በመኖሪያ ቤቶችም እየዞረ ሂጃብ ላይ ጥቃት ከፍቷል፡፡ የኢድ አል አድሀ በዓልን ለማክበር ለኡዱህያ ብለው ያረዱም በመንግስት ተከሰው ዘብጥያ ወርደዋል፡፡ መንግስት ማንኛውንም የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በመቆጣጠር እሱ ባሰመራት ጠባብ ክብ መስመር ውስጥ ለማጠር በመሞከር፣ ሙስሊሙ መንግስት እየዘገነ የሚሰጠውን ብጭቅጫቂ ነፃነት ብቻ ተጠቅሞ ከመንፈሳዊውም ሆነ ከማህበረ-ኢኮኖሚያዊው የህይወት ዘርፍ እንዲገለል የማይሳካ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ አለባበስን ጨምሮ የአምልኮ ተግባራትን ሁሉ በመቆጣጠርም በመንግስት በጎ ፍቃድ የሚቸሩና ባስፈለገ ሰዓት የሚከለክላቸው ተግባራት በማድረግ የጭቆና ማዕቅፍ ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡
ሙስሊሞች ለውዱ ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ያለንን ጥልቅ ፍቅር በተለያዩ መልኮች የምንገልፅ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱም ‹‹እናትና አባቴ መስዋዕት ይሁኑልዎ›› የሚለው የፍቅር መግለጫ ቃል አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ከኢስላም ቀደምት ታሪክ አንስቶ ያለና የነበረ አገላለጽ በአረብኛው ሲተረጎም ‹‹ፊዳከ›› የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን በዒድ አል አድሐ ሰላት ወቅት መንግስት ይህንን ፍቅርን ብቻ ገላጭ የሆነ ሐረግ የተጻፈበትን ቲሸርት የለበሱ ወጣቶችን በግፍ በማሰር የስርዓቱን እስልምና ጠልነት አመላክቷል፡፡ ሙስሊሞችን ለመጨቆንም በርካታ ህገ-መንግስታዊ መርሆዎችን በመናዱ ተግባር እንደሚቀጥል አረጋግጦልናል፡፡ የዜጎችን የእምነት መብት መጨፍለቁ ሳያንሰውም ‹‹የምትለብሱትንም እኔ ነኝ የምመርጥላችሁ›› በሚል ፈሊጥ የፀብ አጫሪነት ጎዳናን መምረጡን ቀጥሏል፡፡
ካሁን ቀደም ደጋግመን ግልጽ ስናደርግ እንደቆየነው ሁሉ ዛሬም ‹‹የእምነት ነፃነታችንን በህገ-መንግስቱ መሰረት እናስከብራለን!›› በሚል መርህ የጀመርነው ህዝባዊ ትግል መብቶቻችን በሙሉ እስኪከበሩ የሚቀጥል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ብሄራዊ የሃይማኖት ጭቆናን ለመታገልም ሁሉንም ሙስሊም በሚያሳትፍ የትግል ጥላ ስር በመሰባሰብ እስካሁን ከከፈልነው መስዋእትነት ባሻገር የተሟላ ነፃነት እስክናገኝ ድረሰ አስፈላጊውን መስዋእትነት በአስፈላጊው ቦታና ጊዜ እየከፈልን ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ ‹‹ትግላችን አስከ ድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል!›› ለእኛ መፈክራችን ሳይሆን የመብት ትግላችንን ያዋቀርንበት ታላቅ መርሃችን ነውና!!!
ብሄራዊ ጭቆናን አንቀበልም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!