የፍቅር ጠባሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


broken heart
አሜሪካ ከመጣ ረጅም አመታት ተቆጥረዋል። ታዋቂና ተወዳጅ ድምፃዊ ነው። ከፍቅረኛው ጋር በአብሮነት እየኖሩ እያሉ ከአመታት በፊት አንድ ነገር ይከሰታል። ድምፃዊው ለመድረክ ስራ ፍቅረኛውን ተሰናብቶ ወደሌላ ስቴት ለመሄድ ሬገን አየር ማረፊያ ይደርሳል። በእለቱ ሃይለኛ ስኖው ይጥል ስለነበረ በረራዎች ይሰረዛሉ። ወደፍቅረኛው ደውሎ ሊነግራት ሲሞክር ስልኳ ዝግ ነው ይላል። ቤቱ ደርሶ ወደመኝታ ክፍሉ ሲያመራ ..ፍቅረኛው በገዛ አልጋው ከአንድ ሃበሻ ጋር ስትዳራ እጅ ከፍንጅ ይይዛታል። ምንም ሳይናገር አብረው በፍቅር መቀጠል እንደሚችሉ ገለፀላት። ለሁለት አመት ቀጠሉ። “ቀዝቃዛው በቀል” እሷን ምን ያክል እንደሚጐዳት ለማወቅ የግድ እሷን መሆን አያስፈልግም። ድምፃዊው ስለደረሰበት በደል በአልበሙ ሁለት ግጥምና ዜማ ሰርቶ አቀንቅኗል። ዘፈኖቹ አስደናቂ ናቸው!! ..ልጅ ሳይወልዱ ከሁለት አመት በኋላ ተለያዩ። ከዚህ ምን እንማራለን?