መንግስታዊ ሕገወጥነት ተጠናክሯል::ወያኔ የፋይናንስ ጥያቄውን ሊጨብጠው አይደለም ሊዳስሰው አልቻለም::(ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


መንግስታዊ ሕገወጥነት ተጠናክሯል::ወያኔ የፋይናንስ ጥያቄውን ሊጨብጠው አይደለም ሊዳስሰው አልቻለም::(ምንሊክ ሳልሳዊ)

በፋይናስ ባዶነት የሚሰቃየው ወያኔ የሚሰበከው እድገት ለፕሮፓጋንዳዊ የሚዲያ ፍጆታ ብቻ መሆኑ ተረጋግጧል::ከዲያፖራው የተጠየቀ ገንዘብ አልተገኘም ያሉት (ዶክተር?)ዸብረጺሆን ከመንግስት ሰራተኛው አስገድደው እየመነተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል::ወያኔ የፋይናንስ ጥያቄውን ሊጨብጠው አይደለም ሊዳስሰው አልቻለም::በፕሮፓጋንዳ ብቻ ተታለው በኢንቨስትመንት እንሰማራለን ብለው የመጡ የውጭው አለም ሰዎች በቢሮክራሲው መንተክተክ የተነሳ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ትብብር ማግኘት አለመቻላቸውን በሙስና ውስጥ እንዲሰሩ በመጠየቃቸው ከመናገራቸውም በላይ የጀመሩት ኢንቨስትመት እንደሚቋረጥ የወያነ ባለስልጣናት እንደሚያስቆሟቸው እና ለምን ሲሉ መልስ የሚሰጣቸው አከል እንደሌለ እና ጨረታ ካሸነፉ በኋላ እንደሚሰረዝ ለማን እንደሚሰጥ እንደማያውቁ አማረው እየተናገሩ ነው::

የሃገር ውስጥ ታዋቂ ነጋዴዎችን ጨምሮ የወያኔ ባላባቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያሸሹ መሆኑ ነው::የተረፈ ካለ ደሞ ወደ ባንክ ከመውሰድ ይልቅ በእጅ መያዝ እየተመረጠ መጥቷል::አገር ውስጥ ደሞ ከማስቀመጥ ይልቅ ውጪ አገር መላክ እየተለመደ መቷል::አገር ውስጥ ባለው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ተጨማሪ ጉልበት ሊፈጥር የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም ውጭ እንዲቀር እየተደረገ ነው፡፡ የገባ ካለም ባለስልጣናት ባቋቋሙት ቡድን በጥቁር ገበያ እንደገና እንዲወጣ እየተደረገ በመሆኑ አገሪቱ ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም፡፡ ይህ የሚያመለክተው ዜጎችም ይሁኑ የአገዛዙ ሹሞች በፖለቲካው ጉዞ ላይ እምነት እንዳሌላቸው ሲሆን እየተሽመደመደ እና እየደቀቀ ያለው የፖለቲካ ስርኣት ምንም ለውጥ ሊያመጣ አለመቻሉ ኝጹሃን ሰዎች በወንጀለኝነት ሳይሆን በአስተሳሰባቸው ወህኒ መውረዳቸው የፈጠረው ስጋት ነው::

ዜጎች በህግ ላይ እና በንጽህናቸው ላይ ከመተማመን ይልቅ የህግ የበላይነት ከመጥፋቱ አንጻር እጅግ ፍርሃት ውስጥ በመግባታቸው የተማሩ እና በንግዱ አለም የተሰማሩ ሁሉ በፍርሃት ከመርበድበዳቸው እና ከመሰደዳቸው በላይ አሉ የተባሉትም ወያኔ በሙስና ባልደረቦቹ ላይ ፖለቲካዉ ገጀራ ሲያሳርፍ እየተመለከቱ ስራ በማቆም ከመደናበራቸውም ሌላ በራሳቸው አለመተማመን ያለባቸውን ጨምሮ በሙስናው ከባለስልጣናት ጋር የተነከሩ ሲሆን ሌሎች ደሞ እስከሚጣራ ለምን ልታሽ በሚል ባለው የፖለቲካ አመራሩ ላይ እምነት በማጣት የንግዱን ስራ ጥለውት ከሃገር በመሸሽ ላይ ናቸው::

የንግድ ስራዎች ከፓርቲ ድርጅቶች ውጭ በጣም ተዳክመው እና ሞተው ያሉ ሲሆን ዲያስፖራው ለቤተሰቡ ከሚልከው የውጪ ምንዛሬ ገንዘብ ከሚገኘው ገቢ ድጋፍ በስተቀር የገንዘብ እንቅስቃሴዎች ጭራሽ ገደል መግባታቸውን እና ደንበኞች በባንኮች ላይ ያላቸው አመነታ በመጥፋቱ ግንኙነቶች መልፈስፈሳቸው በይበልጥ ለግል ባንኮች መዳከም ምክንያት ሆነዋል ሲሉ ይህ ደሞ የገንዝብ እንቅስቃሴውን ገድሎታል::በጣም ድብን ያለ እውነት ነው::በውጭ ምንዛሪ ችግርና እጥረት ምክንያት በጣም የሚያስፈልጉ ዕቃዎች እንደተለመደው ከውጭ እየገቡ አይደለም፡፡ በጥቂቱ የመጡ ካሉም ዋጋቸው የማይቻል እየሆነ ነው፡፡ መንግስታዊ ሕገወጥነት ተጠናክሯል::ወያኔ የፋይናንስ ጥያቄውን ሊጨብጠው አይደለም ሊዳስሰው አልቻለም:: #ምንሊክሳልሳዊ