ዳግማዊት ማ.ሌ.ሊ.ት – በሃገራችን ኣጋጥሞ ያለው ኣሰቃቂ ድርቅ ፈጣን ምላሽ ካላገኘም ለታላቅ እልቂት ሊዳረግ እንደሚችል ግልፅ ሆነዋል።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ዳግማዊት ማ.ሌ.ሊ.ት Amdom Gebreslas
****************
በኣሁኑ ወቅት በሃገራችን ኣጋጥሞ ያለው ኣሰቃቂ ድርቅ 8.2 ሚልዮን ህዝብ እጆቹ ለተመፅዋችነት እንዲ ዘረጋ፣ ፈጣን ምላሽ ካላገኘም ለታላቅ እልቂት ሊዳረግ እንደሚችል ግልፅ ሆነዋል።
ይህ ኣስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልገው የህዝብ ቁጥር በሳምንታት ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት ሽቅብ እየጨመረ ነው።
በኦሮምያ፣ ዓፋር፣ ሶማሌ ያለው ስፋትና የሚያደርሰው ጉዳት ኣስቀድሞ ታውቆ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በውስን መልኩም ቢሆን እየተሰሩ ናቸው።
በተቃራኒው በኣማራና ትግራይ ክልሎች ስላጋጠመው ድርቅ ግልፅ በሆነ መልኩ መግለጫም ይሁን መብራርያ ሲሰጥ ኣልተስተዋለም።
በተለይ “ቁጥሮችን ያንቀጠቀጠ(የደፈረ) መንግስት” በሚል ቅጥያ የሚታወቀው የትግራዩ ህወሓት መራሽ መንግስት ባለፈው ዓመት “ከክረምት ምርት 38 ሚልዮን ኩንታል፣ በበጋ መስኖ 75 ሚልዮን ኩንታል እህል ኣመረትኩ ” በሎ እንኳን ለመግለፅ ለመስማትም የሚከብዱ ሪፖርቶች ሲገልፅ ትንሽ እፍረት እንኳን ኣልተሰማውም ነበር። ተዋረድ ሲለው የዘንድሮ ድርቅ ተከሰተ።
ድርቅ የሚቋቋም ኢኮኖሚ ሳይገነባ ግዜው በስብሰባና ድግስ እንዲሁም የዳታ ክምሮች ሲጋግር ያባከነው መንግስት ህዝቡን በረሃብ እያስጨረሰው ነው።
ገና መስከረም ወር ጀምሮ በረሃብ መሞት የጀመረው በኣሁኑ ሰዓት ኣስከፊ ደረጃ መድረሱ እየሰማን እያየን ነው።
በረሃብ ሞቱ የሚባሉ ሰዎችና በሞት ኣፋፍ የሚገኙ ሰዎች ስም ዝርዝር እየደረሰን ነው። የገበሬዎች እንስሳት እየወደቁ ነው።
መንግስት ከየቦታው ሪፖርቶቹ እየደረሱበት ቢሆኑም ሰምቶ እንዳልሰማ እየሆነ ነው።
በድምፂ ወያነ፣ ኤፍኤም ሬድዮዎች፣ የቲቪና በጋዜጦች መንግስት ድርቁ በቁጥጥር ስር እንዳዋለው እየለፈፉ ይገኛሉ።
እውነታው ግን ይህ ግዜ በሚልዮን ለሚቆጠር ህዝባች ክፉ ቀን ነው።
የደቡባዊ ዞን፣ የደቡብ ምስራቅ፣ የምስራቃዊ፣ የምዕራባዊ ዞኖች ኣብዛኛው ወረዳዎች፣ የማእከላዊና የሰሜን ምዕራብ ዞኖች የተወሰኑ ወረዳዎች በድርቅ ተመትተዋል። ደህና ዝናብ ያገኙ ወረዳዎችም የበረዶና የጎርፍ ኣደጋ ኣጋጥሟቸዋል።
ስለዚህ እርዳታ የሚጠብቅ የትግራይ ህዝብ የጠቅላላ ህዝቡ ግማሹ ይሆናል። ኣጠቃላይ ተረጂ የሚታዉቀው እስከ ጥር ወር ቢሆንም ኣሁን ባስቸኳይ የእርዳታ እጆች የሚጠብቅ ህዝብ ግን ከኣንድ ሚልዮን ህዝብ በላይ ነው።
ድርቁ በተመለከተ በፃፍኳቸው ፅሁፎች ኣጋነንክ፣ ውሸት ነው፣ ክፉ ኣትመኝ ወዘተ የሚሉ ወገኖች ኣጋጥመውኛል። ይሁን እንጂ የኣደጋው ስርጭት ሰፊና ኣደገኛ በመሆኑ ለመግለፅ ቅር እያለኝም ቢሆን ስለ ኣደጋው እያሳሰብኩኝ እገኛለው።
የትግራይዋ ህወሓት ግን እስከ ዛሬ 05 / 02 / 2008 ዓ/ም ስለ ድርቅ ግልፅ የሆነ መግለጫ እንኳን ልትሰጥ ኣልቻለም ነበር።
የትግራይ ክልል እርሻ ቢሮ ዛሬ ዓርብ ጥዋት በሬድዮ FM መቐለ ፋና የትግርኛ ፕርግራሙ ፈራ ተባ እያለ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከመግለጫው ለመረዳት እንደሚቻለው ኣምና ሚልዮን ኩንታል ኣመረትን ያለው ኣንደበታቸው ተቃራኒውና መራር ሓቅ ለመቀበልና ስለ ኣጋጠመው የድርቅ ኣደጋ ለመግለፅ እንደማይፈልጉ ነው።
በመግለጫቸው 889,000 ( ስምንት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ) ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ እንደሚጠብቅ ገልፀዋል።
ለዚህ ኣንድ ሚልዮን የሚጠጋ ህዝብና ለእንስሳቶቹ የሚሆን በጀት ተመደበ ብለው የገለፁት ገንዘብ 100 ሚልዮን ብር ብቻ ነው። በሃገር ደረጃ በድርቅ ለተጠቁ ወገኖች መርጃ 4 ቢልዮን ብር እንደተመደበ መገለፁ የሚታወስ ነው።
ለትግራይ ተመደበ የተባለው በጀት ከሚያስፈልገው ወቅታዊ ብር 2.5 % ብቻ ነው።
ከ8.2 ሚልዮን በድርቅ ተጠቂ የሆነ የሃገሪቱ ህዝብ የትግራይ ክልል ድርሻ 11% ነው።
ያለ እርዳታ እንዲቀሩ የተፈረደባቸው የትግራይ ሰዎች 97.5% ናቸው። ይሄ ህዝብ እሚቀመስ እሚላስ እንደሌለው እየታወቀ ከእርዳታ መገለሉ ሞት ተፈረደበት ማለት ኣይደለምን?
ከሁሉም በላይ ህወሓት በድርቅ ለተጠቃው ህዝብ የሚያስፈልገው ኣጠቃላይ በጀት በግልፅ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ኣሻፈረኝ ማለቷ በ77 ፈፀመችው ለሚባለው ክህደት የሚደግም ፀያፍ ተግባር ነው።
እነ ዶ/ር ግደይ ዘርኣፅዮን፣ ገብረመድሂን ኣርኣያ ለቢቢሲ(BBC) የሰጡት መግለጫ ህወሓት/ማ.ሌ.ሊ.ት/ በትግራይ ህዝብ ስም በዓለለማችን ታዋቂ ኣርቲስቶች የተሰሰበሰበው የእርዳታ ብር ለተረጂዎች እንድታደርስ ተቀብላ 95% ለራስዋ ወስዳ የቀረው 5% ብቻ ለህዝቡ እንደሰጠች ነው።
ይህ ፍፃሜ ከወቅቱ የተመደበ ባጀት( የሚያስፈልገው መጠን) ይፋ ኣለማድረግዋና የ77ቱ የህወሓት ድርጊት ስናስተያየው ተኣማኒነት እንዲያገኝ ኣስተዋፅኦ ያደርጋል።
እንደ የድሮ የህወሓት ታጋዮች ሃሳብ ከሆነ ኣቶ መለስ የሚመሯት ማ.ሌ.ሊ.ት(ማርክሲስት.ሌኒንስት. ሊግ .ትግራይ) ለእርዳታ የመጣው ብር ለመመስረቻ በዓልዋና ለጦር መሳርያ መግዣ እንዳዋለችው የሚታወቅ ሲሆን ባለፈው ኣመት ለተከበረው 40ኛው የምስሩታ በኣል ላወጣችው 2 ቢልዮን፣ ለዲያስፖራ ቀን ያወጣቹ 200 ሚልዮን ብር ማካካሻ እንዲሆናት ከህዝቡ ጎሮሮ ለመንጠቅ የሚመጣው እርዳታ እየተጠባበቀች ያለች ያስመስልባታል።
“…ሲሰርቅ ያየሁት ሲሰጠኝ ኣላምነውም…” እንደሚባለው መንግስትነቷ በነፍጧ ያረጋገጠችው ህወሓት በድርቅ 1977 ዓ/ም ለተረጂዎች የመጣ ገንዘብ ከ95% በላይ ከህዝቡ ጎሮሮ ነጥቃ ለራሷ እንዳዋለችው ስናውቅ ዘንድሮም ማለሊታዊ ተግባርዋ ኣብሯት እንዳለ እንረዳለን።
በትግራይ እርዳታ ለማግኘት የሚያስችልቱ መመዘኛዎች የድርቁ ኣደጋ፣ የበረዶና የጎርፍ ኣደጋ ሰለባ መሆን ብቻ በቂ ኣይደለም።
የመዳበርያ ዕዳ መክፈል፣ የምርጥ ዘር ክፍያ መመለስ፣ የደደቢ ብድርህ መመለስ፣ የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ኣባል መሆን ፣ የተቃዋሚ ድርጅት ኣባልና ደጋፊ ኣለመሆን ሲሆኑ ፣ ከወረዳና ቀበሌ ባለስልጣን ኣለመጣላትም ይጠብቅብሃል።
ከነዚህ ውጭ ከሆንክ የምታገኘው እርዳታ ኣይኖርም። የትግራይ ህዝብ በሃይለስላሴና በደርግ ግዜ እንዳደረገው ቤቱን ጥሎ ሂወቱ ከሞት ለመታደግ መሰደድና መለመን ዕጣው ይሆናል።
ህወሓት ድርቅ ሊቋቋም የሚችል ብቁ ፖሊሲ ኣበጅታ ኣደጋው ለመከላከል ባለ መቻልዋ በመጀመርያ የሚያስጠይቃት ሲሆን፣ ኣደጋው ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ ኣደጋ ማድረስ ሲጀምር ኣስቸኳይ የመከላከል ስራ ባለመስራትዋ እየጠፋ ባለው ሂወትም ችሎት ላይ መቆም ኣለባት።
ኣደጋው ለመደበቅ የሞከረችው ሳይበቃት እርዳታው ለፖለቲካዊ ጥቅም በማዋልዋም በሂወት ልትጠየቅ ይገባል።
ድርቁ ህወሓት በተግባርዋ ዳግማዊት ማሌሊት መሆንዋ በደምብ የተወነችብትና ያረጋገጠችበት ኣጋጣሚ መሆኑ እያረጋገጠችልን ነው።
የወገናችን ሂወት እናድን። ተደብቆ የሚሞት ሰው ሊኖረን ኣይገባም።
ነፃነታችን በእጃችን ነው…!
IT IS SO……!



