ይሄ ነገር ዘረኝነት ይሆን እንዴ፡) (አሌክስ አብርሃም)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ዛሬ ወደአንድ ሆስፒታል ጎራ ብየ ነበር ….(አይዞን በሰላም ነው) እና የገረመኝን ነገር አስተዋልኩ ባለቤቱን ጨምሮ አራት ዶክተሮች አሉ አራቱም ከአንድ ብሔር የወጡ ለመሆናቸው የአነጋገራቸው ቅላፄና ስማቸው ይገልፃል …. የገረመኝ ይሄ አይደለም ነርሶቹ ሁሉም በሚባል ሁኔታ ከአንድ ብሄር የወጡ መሆናቸውን ማወቅ ቀላል ነው … እንደውም እርስ በእርስ ሲነጋገሩ ሁሉ የወጡበት ብሔር ቋንቋ በመሃል ቀልቀል ያደርጋሉ … ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች …ፅዳት ሰራተኞች አብዘሃኞቹ ከአንድ ብሔር የወጡ ናቸው . . .የአንቡላንስ ሹፌሩ ሳይቀር …ጥያቄው ለምን የአንድ ብሄር ሰዎች አንድ ሆስፒታል ውስጥ ተሰበሰቡ ሳይሆን በግልፅ ቅጥር በግልፅ ቅጥርና ደንብና ስርአት ትመራለች የምትባል አገር ላይ ከዚህ ሁሉ ሽ ከሚሊየን ጎሳና ነገድ ተነጥለው ከአንድ ሰፈር ሰብሰብ ብለው የህዝባችንን ጤና ለመጠበቅ ሲተጉ ብቻቸውን አይፈሩም እንዴ ብየ ነው፡)
በጣም የገረመኝ ታዲያ ምን መሰላችሁ ሊታከም ተራ ከሚጠብቀው ህመምተኛ ውስጥ አብዘሃኛው ከዚሁ ብሔር የወጣ ታካሚ ነው ….(የበሽተኞች ስብጥር ይከበር ብየ አልጮህ ነገር በሽተኛ አዋጡ ብሎ ብሄር ብሄረሰቦችን ማስቀየም ይሆንብኛል ብየ ፈራሁ) የቀልዱ ቀልድ ነው ….. ግን እኔ ይሄ ነገር እየሸከከኝ ነው … ከዚህ በፊት ፅፌ እንደነበረው ….አንዳንድ ከእምነት ጋር የማይገናኙ ድርጅቶች ባለቤቱ የሆነ እምነት ተከታይ ስለሆነ ብቻ የዛ እምነት ተከታዮች ከፅዳት እስከስራ አስኪጅ ሲሰበስብ ታያላችሁ ! ጭራሽ የምታዩት ሰው ሁሉ አንድ አይነት እምነት ተከታይ መሆኑን ስትታዘቡ ቤተ እምነት እንጅ ለህዝብ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ድርጅት አይመስላችሁም ! እና ይሄ ነገር ዘረኝነት ይሆን ወይንስ ተመሳሳይ እምነት እና የትውልድ ቦታ ያላቸው ሰዎች በተፈጥሮ መሳሳባቸው የፈጠረው ጉዳይ ….እንጃ ! ግን እንደአስተያየት በማንኛውም ጉዳይ ቢሆን ብቃት ያለው ተወዳዳሪ ድርጅት ለመመስረት ማንኛውም የስራ ቅጥር ….(((ችሎታና ችሎታ ላይ ብቻ))) ያነጣጠረ ቢሆን መልካም ነው ባይ ነኝ !!