እናት ለብድር
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አርአያ ተስፋማሪያም
ዲሲ በሚገኝ የሃበሻ ሬስቶራንት ተቀምጠን ስናወጋ አንዲት ነጭ መኪና የምታሽከረክር ወጣት ከደጃፍ ደርሳ ቆመች። በአብዛኛው የሰውነት ክፍሏን የሚያሳይ ልብስ ቢጤ ጣል አድርጋለች። ስልኳን እየነካካችና እየተመናቀረች ዘለቀች። …ከውስጥ አንዲት እናት ወጡ። እድሜያቸው 60 ያልፋል። ቀጭንና ጠይም የሆኑት እናት ሁሌም አንገታቸውን ያቀረቀሩና ዝምታን የሚያዘወትሩ በመሆኑ ..አንጀቴን ይበሉኛል። ወጣቷን በግርምት እያዩዋት ተጠጉ። «ነገ የምሰጥሽ 100 ዶላር..ሙች እሰጥሻለሁ…እመኚኝ.» እያለች እጃቸውን ይዛ ትማፀናለች። «ነገሩ አትሰጭኝም…አውቀዋለሁ..ለዛ ለሺሻሽ ነው» አሉና ከማብሰያ ክፍል አምጥተው ገንዘቡን ሰጧት። እየተጣደፈች ወጥታ ሄደች። «ልጆዎ ናት?» ስንል ጠየቅናቸው። «አዎ፤ ምን ዋጋ አለው። ስራ አትሰራ፣ ወይ አትማር። ይህን ሺሻ የሚባል ሌት ተቀን ስትምግ ትውላለች። እኔ እንጀራ ጋግሬና እሳት ፈጅቶኝ የማመጣውን ትወስድና ለሱሷ ታደረገዋለች። የሰው መኪና እያሽከረከረች የሃብታም ልጅ ለመምሰል ትሞክራለች። ወንዱ ልጄ ጐበዝ ነው። ገንዘብ አልሰጥሽም ስላት “ራሴን አጠፋለሁ” እያለች ታስጨንቀኛለች። ወልዳ ታግኘው!» አሉ።