ላይ የነፃነት ትግል የጀመሩበትን 54ኛ ዓመት በዓል በኢትዮጵያ ምድር እየደለቁና እየጨፈሩ ሲያከበሩ የነበረውን ጭፈራ እንደ ቀዳሚ የዕለቱ ታላቅ ዜና ሲያቀርብ በቁጭት በመመልከቴ ነው፡፡ ይኼ ቴሌቪዥን ጣቢያ የማን ነው? ብዬ እራሴን ጠየቁኩ፡፡
የቴሌቪዥን ጣቢያችን የጭፈራውን ዜና ሲያቀርብ የቀረው ነገር ቢኖር ኤርትራውያኑና የኢሕአዴግ መሪዎች እንደሚለፍፉት ከኢትዮጵያ የባርነትና የቅኝ ተገዥነት ነፃ ለመውጣት ኤርትራውያን ትግል የጀመሩበትን 54ኛ ዓመት አከበሩ በማለት እንኳን ደስ ያላችሁ ብሎ መለፈፍ ነበር፡፡
ከቁጭቴ በመነሳት ለእናት ኢትዮጵያ ክብር የሚያስብና የሚቆረቆር መንግሥት የለም ወይ? ብያለሁ፡፡
ከዚህ በፊት ሻዕቢያ ኤርትራን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ድረስ፤
-የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ሰጠናቸው እያሉ የቀለዱብን፣
-በሪፈረንደሙ ጊዜ በራሳችን ምድር በግልጽ የጨፈሩብን፣
-ከነፃነት በኋላ በመጀመርያዎቹ ሁለትና ሦስት ዓመታት የአዲስ አበባን የቀበሌ አመራር ይዘው የቦረቁብን፣
-የወያኔ መንግሥት ሆነ ብሎ ስላሞላቀቃቸው እኛ ኢትዮጵያውያን ሁለተኛ ዜጋ ኤርትራውያኖች ግን አንደኛ ዜጋና ባለመብት የሆኑበት፣
-በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እስከ ሚኒስትርነትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ቁልፍ ቦታዎች የሰጠናቸው፣
-በ1983 ዓ.ም. ሻዕቢያ ከወያኔ ጋር በመሆን አዲስ አበባ ሲገቡ ጎተራ አካባቢ የነበረውን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በማፈንዳትና በማቃጠል በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ሊያደርሱ የነበረውን ስቃይ፣
-በኢትዮ የኤርትራ ጦርነት የተከፈለው የጀግኞች ልጆቻችን መስዋዕትነት፣
-በመንግሥታችን የኢትዮጵያዊነት ስሜት ማጣት ኤርትራውያን የፈለጉትን መረጃና ሰነድ ከአገራችን እንዲወስዱ የተደረገው ተባባሪነት፣
-ኤርትራ የግላችን ኢትዮጵያ የጋራችን (የሁላችን) ተብሎ የተቀለደብን፣
-ኤርትራውያን ሥልጡኖች ኢትዮጵያዊያን ፈሪና ኋላ ቀሮች ተብለን የተሰለቀብን፣
ሳያንስና ሳይረሳ አሁን በራሳችን ቴሌቪዥን ጣቢያ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል 54ኛውን የነፃነት ትግል የጀመርንበት መታሰቢያ ክብረ በዓል ብለው ይጨፍሩብን እንዴ? እጅግ የሚያሳዝንና የሚያቆስል ድርጊት ብቻም ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡ ለአገር ክብር የቆመና ለኢትዮጵያ የሚቆረቆር መንግሥት አለን ወይ? የሚያስብል ነው፡፡ አሁንም መንግሥታችን የሻዕቢያ ጉዳይ ፈጻሚና ተላላኪ ነው ወይ? ከማስኘት አልፎ የቴሌቪዥን ሥርጭቱን ማቅረብም ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ቁስለት ነው እላለሁ፡፡
ነሐሴ 27 ቀን 2007 በወጣው ሪፖርተር ቁጥር 1601 ‹‹ታክሲ›› ዓምድ ላይ ‹‹እንዲህማ አይጨፈርብንም፤›› በሚል ርዕሰ ከቀረበው፣ ለዛና ቁም ነገር ካለው የታክሲ ውስጥ ጭውውት ተሳፋሪ አዛውንት እናት ለአንድ ወጣት የቴሌዥኑን ሥርጭት አስመልክቶ በቁጭት ያስልተላለፉትን የሚከተለውን መልዕክት ልቤ እየነደደ ነው ያነበብኩት፡፡
‹‹ይኼንን ቴሌቪዥን አላየህም? የሻዕቢያ ተላላኪዎች በስደተኝነት ስም ሲደነፉበት፡፡ የስንትና ስንት ወገኖቻችንን ደም የገበርንበትን የአገር አንድነት ተጋድሎ ሻዕቢያ በጓሮ በር ሲያራክስብን አላየህም? በወኪሎቹ አማካይነት የመገንጠል ጦርነቱን 54ኛ ዓመት በገዛ ቴሌቪዥናችን እየደነፉ ሲያከብሩበት አላየህም?›› ሲሉት ‹‹እንዲህማ አይጨፈርብንም›› ብሎ ወጣቱ በቁጭት ደነፋ፡፡
ይኼ አናዳጅ መልዕክት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቢተላለፍም ጥቂትም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ አገራቸው ልዩ ፍቅር ያላቸው ኤርትራውያንን በአክብሮት ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ እንደ ብርቅ ከምጠቅሳቸው፣ ለኢትዮጵያ መስዋዕት ከሆኑ ውድ የኤርትራ ጀግኖች መካከል ለዘርዓይ ደረስ፣ ለአብረሃም ደቦጭና ለሞገስ አስገዶም ትልቅ አክብሮት አለኝ፡፡ ኢትዮያዊነት ዜግነታቸውን ይዘው ለቆዩ የኤርትራ ልጆች ልዩ ወንድማዊ ፍቅሬን እገልጻለሁ፡፡ የመንግሥት ኃላፊነት በአገር መቀለድ አይደለም፡፡ ለኢትዮጵያ የሚቆረቆር መንግሥት እንፈልጋለን፡፡ ተጠያቂነት ይኑር በአገር አይቀለድ፡፡