*** ምስጢር ነው!*** Tigist Alemneh
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጌታዬ!

ላንተ ያለኝ ፍቅር
ላንተ ያለኝ ክብር
ምን ያህል እንደሆን…
ተወው አልነግርህም ብትሆንም ኩራቴ
ምስጢር አርጎት ይቆይ ልጉም አንደበቴ።
ስላንተ ‘ሚያወራ የሚናገር አፌ ሰውን ካበሳጨ
የፍቅሬ ጥግጋት በቃላት ተሰፍሮ በክፉ ካሳጨ
ይቅር አልነግርህም……
እስካልቆረቆረኝ የተፈናጠጥኩት የፍቅርህ ኮርቻ
ዝም………… ብዬ ልውደድህ በልቤ ውስጥ ብቻ።
ለምን እንዳፈቀርኩ ስለምን ልናገር በቃላት ጋጋታ
ስትወደኝ መውደዴ ተስሎ እየታየ በፊቴ ገፅታ።
“ከ‘ኔ ‘ሚበልጥ የለም” የሚል ባለጊዜ ጉልላቴን ይዞ
እንደ ክፉ ቁራ የጎጆየን ክዳን ሰንበሌጧን መዝዞ
በሽንቁር እያየኝ…
“ብትወጅኝ ይሻላል!” ብሎ እያስፈራራ
አንተን እንደወደድኩ እንዴት ብዬ ላውራ?
የለም አልነግርህም!
ባላንጣህ ክፉ ነው ያለቅጥ ቂመኛ
አንተን እያጥላላ ገዝቶልኝ ደመኛ
ስጦታ እንደሰጠኝ ፍቅርን ከኔ ይሻል
እኔ አንተን እያሰብኩ ይነጋል ይመሻል።
ከሚያቃጥል ፀሐይ ከሚበትን ነፋስ
ቁሞቀር እያለ ከሚያሳቅቅ ምላስ
በሞገሳም ጥላህ ሀገር የሸፈንከው
ሊደፍረኝ ከመጣ ክብሬን የታደከው
የኔ ጀግና አንተ ነህ ልቤን የማረከው።
ፍቅሬ እንዲሁ አይደለም ምክንያታዊ ነው አንግሼው ይኖራል
ለሰጠኸኝ አንተ ላንተው እንደሆነ ዘመን ይሻገራል።
ጌታዬ አልነግርህም ዝም……… ብዬ ልውደድህ
ለ‘ኔ ባፈሰስከው በዛ ንፁህ ደምህ
ያኔ ባበጀኸው በፍቅር መንገድህ
ባላንጣህ እሾሁን ዘርቶበት እያየሁ
ጋሬጣውን ጥሼ እንደምን አልፋለሁ?
ያው እንደነገርኩህ……
ምስጢር ስለሆነ እ ወ ድ ሃ ለ ሁን ዛሬ ላይ አልልም
ጊዜ የማይሽረው ፍቅሬን አልነግርህም።
ጣይቱ ሆቴል
17/05/2007
