በትግራይ ክልተ ኣውላዕሎ የህዝባ ቁጣ ተቀሰቀሰ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የመንግስት ኣካላት ይሁኑ ኣይሁኑ ለህዝቡ ግልፅ ያልሆኑ ኣካላት በክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ የሚገኘው የዮዲት ጉዲት ( ጋዕዋ ) መቃብርና በዙርያው የሚገኙ ተዛማጅ ቅርሶች ወዳልታወቀ ቦታ ነቅለው ሊወስዱ ሲሞክሩ ከኣከባቢው ህዝብ ጋር ተጋጭተዋል።
መቃብሩ የሚገኝበት ወረዳ ክልተ ኣውላዕሎ፣ ኣይናለም ቀበሌ፣ ዓዲ ኣካውሕ ሰፈር ኑዋሪ ህዝብ በዝርፍያው ክፉኛ ተቆጥቶ ነቀላው ከሚያካሂዱ ኣካላት ተጋጭቶ ኣናስፈርስም በማለት ኣስቁማቸዋል።
የኣይናለም ነዋሪ ህዝብ የዮዲት ጉዳት መቃብርና በዙርያው ለዘመናት በቅፉ ኣምቆ ያቆያቸው ቅርሶች ከኣከባቢው ተዘርፈው እንዲጠፉ ፍቃደኛ ሊሆን ኣልቻለም።
የዮዲት ጉዲት( ጋዕዋ ) መቃብር ከኣመታት በፊት ከቱሪዝም ቢሮ የመጡ ባለሞያዎች ህዝቡን ሰብስበው ” የዚህ ታሪካዊ ቦታ ቅርሶች የትግራይ፣ የኢትዮጵያ ብሎም የዓለም ማህበረሰብ ሃብት ናቸው። በኣሁኑ ሰዓት ቅርሱ ኣውጥቶ፣ ኣጥንቶ ማልማት የተማረ የሰው ሃይልና በቂ ገንዘብ ስለሌለን ኣቅም ተገኝቶ እስከምናለማው ነቅተህ ጠብቀው…” የሚል መልእት በመነገሩና በመያዙ እስካሁን በደምብ ጠብቆታል።
የህዝቡ ቁጣ የተነሳው ሓሙስ 27 / 01 / 2008 ዓ/ም ጥዋት ማንነታቸው የማይታወቁ ኣራት መኪኖች ይዘው የመጡት ሰዎች ቅርሶቹ ኣውጥተው ወዳልታወቀ ቦታ ለመውሰድ ሲሞክሩ የዓዲ ኣካውሕ ሴቶች ተሰባስበው ኡእታቸው በማሰማት ኑዋሪዎቹ በመሰባሰብና ከበው በመያዝ ያከባቢው ህዝብ እንዲሰበሰብ በማድረግ ቅርሱ ከመወሰድ እንዳዳኑት ይገልፃሉ።
የቀበሌው ህዝብ ሰወቹ ይዞ ወደ ቀበሌው የፀጥታ ሰዎች ያስረከባቸው ቢሆንም ሰዎቹ ከወረዳው ባለስልጣኖች በመነጋገር ተለቀዋል።
ሰዎቹ “የክልል የቱሪዝም ሃላፊዎች ናቸው” የሚል ከወረዳ መልእክት የተነገረ ቢሆንም ” እንደሌባ ሸልከው መጥተው ወዴት እንደሚወስዱት ስለማናውቅ ለሺ ኣመታት ተጠብቆ የቆየ ቅርስ ኣሳልፈን ኣንሰጥም፣ ድሮም ሌባ የባለስልጣን ከለላ ተጠቅሞ እንደሚዘርፍ እናውቃለን” በማለት ቅርሱ ኣሳልፈው እንደማይሰጡ ለሶስት ቀን እየተከራከሩ ይገኛሉ።
በጉዳዩ ላይ የህዝቡ ጥያቄ በትግራይ ቱሪዝም ቢሮ የቅርሶች ጥበቃ ሃላፊ ኣቶ የማነ ተደውሎላቸው ” ችግሩ እንዳጋጠመ ኣምኖው ቅርሱ ውቅሮ የተከፈተው ሙዝየም በማስቀመጥ ለጎብኚ ክፍት እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ሲሆን ህዝቡ ሳናነጋግር ወደ ስራ በመግባታችን ለግጭት ተዳርገናል “፣ ከግጭት በሗላም ሃሳቡ በቀላሉ ሊቀበለው ባለ መቻሉ ወደ ግጭት ሊገባ መቻሉ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ኑዋሪዎቹ ተግባሩ “የቅርስ ዝርፍያ” እንደሆነና ሙዝየም ተከፍተዋል የተባለው ” የመብራት ሃይል ኣዳራሽም ራሱ የቻለ ሙስና እየተካሄደበት እንዳለና የድሮ ጀነሬተሮች ሜርኩሪ የተባለ ንጥረ ነገር ስላላቸው ኣውጥተው ለመሸጥ የተዘየደ መላ” እንደሆነና የዮዲት ጉዲት( ጋዓዋ) ቅርሶችም የመዘረፍ እጣ እንደሚያጋጥማቸው ያምናሉ።
ሙዝየሙ ተከፈተ የተባለው ውቅሮ ከተማና ቅርሱ ያለበት ዓዲኣካውሕ ያለው ርቀት ትንሽ ስለሆነ ኣስፈላጊነቱም ህዝቡ ኣላመነበትም።
በዚህ ኣለ በዚያ ህዝቡ ቅርሱን ኣላዘርፍም ብሎ “ሌቦች” ካላቸው ኣካላት ኣንገት ላንገት እየተናነቀ ይገኛል።
የክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ ሃላፊዎችና ኣቶ የማነን ጨምረው ሌሎች በህዝቡ እምነት ያልተጣለባቸው ባለስልጣናትና ህዝቡ ተፋጥጠው ይገኛሉ።
የወረዳው ባለስልጣናት በህዝቡ ተቃውመው እንዲተውና ሃሳቡ እንዲቀበል ማስፈራርያዎችና መደለያዎች እያቀረቡለት ይገኛሉ።
ዮዲት ጉዲት( ጋዕዋ ) በኢትዮጵያ ታሪክ ለኣሱም ስልጣነ መውደም ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበረችና የኣክሱም ታላቁ ሓወልት ያፈረሰች፣ ከወርቅ የታነፀ የኣክሱም ፅዮን ቤተክርስትያን ያቃጠለች፣ በርካታ ቤተ መንግስታትና ኣብያተ ክርስትያናት ያወደመች የኣይሁድ እምነት ተከታይና በሃገራችን ጥቁር ታሪክ ጥላ የተወች ንግስት ናት።
ዮዲት ጉዲት በሃገራችን ለ40 ዓመት ከነገሰች በሗላ በውቅሮ ኣከባቢ እንደሞተችና ዓዲ ኣካውሕ በሚባል ቦታ እንደተቀበረች በታሪክ ተከትቦ ይገኛል።
የዮዲት ጉዲት ( ጋዕዋ ) መቃብርና በዙርያው በከርሰ ምድር የሚገኙ ቅርሶች ተጠብቀው የቱሪስት መስህቦች፣ የምርምር ማእከል ሊሆኑ ያገባል። ያሁኑ መንግስትና ካድሬዎቹ ገንዘብ ኣምላኪ ስለሆኑ ሰርቀው፣ ዘርፈው ሽጠው ባዶ እጃችን ሊያስቀሩን ጫፍ ደርሰዋል።
ቅርሳችን ኣናዘርፍም …! ብለው ከመንግስት ባለስልጣናት ኣንገት ላንገት እየተናነቁ የሚገኙ ወገኖቻችን ልንረዳቸውና ልናግዛቸው ይገባል።
ህዝቡ ያጋጠመው ድርቅ ተቋቁሞ ለቅርሱና ለታሪኩ ያለው ቀናኢነት በጣም ኣስገራሚ ነው።
ህዝቡ ሕንጊዱ ብሎ መዝፈን ጀምሯል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው……!
IT IS SO………!