የወያኔ ባለስልጣናት እና አማካሪዎቻቸው ውሸታቸውን አጧጡፈውታል::እውን የብድር እዳ ክምችት አያሳስብም? (ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


– የኢትዮጵያ ጠቅላላ የብድር መጠን ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወይም ከ1.2 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው::
– የአገሪቱ የብድር ዕዳ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አንፃር ሃምሳ ከመቶ ደርሷል::
– የዋጋ ግሽበት ከሚጠበቀው በላይ የእጥፍ እጥፍ አሻቅቧል::
– በፋይናንስ አቋሞች ላይ ቁጥጥር ባለመደረጉ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ቀውስ ተከስቷል::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የማይሸፈነው የኢኮኖሚ ገበና አግጥጦ ወጥቷል::ከዚህ ቀደም እንደምንለው የወያኔ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተደጋጋሚ ከኪሳራ ውጪ የፈየደው ነገር የለም::ይህ ደግሞ አረቀቅነው ከሚሉ ጀምሮ እያስፈጸምነው ነው ያሉት ድረስ አምነው መስክረውበታል::እቅዱ ስላልተሳካለት ስልጣኑን ለሃገር ገንቢዎች ያስረክብ ድህነትን እንቀርፋለን ብሎ የደሃ ደሃ ፈጥሯል ከዚህም በላይ መጪ ትውልድ ከፍሎ የማይጨርሰው የብድር እዳ እና ሙስና ተንሰራፍቷል;;የሃገሪቷ ኢኮኖሚ አሳሳቢ ነው በዲያስፖራው ድጋፍ እና በአለም ነዳጅ ቅነሳ ተደግፎ ያለ ነው ብለን ሁላችንም ጮኽናል::ሰሚ ባለመኖሩ ጆር ዳባ ልበስ ቢባልም የዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በተራው ፉጨቱን አሰምቷል::

የዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ ያወጡት ሪፖርት እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ የብድር ዕዳ እያሻቀበ በመምጣቱ በብድር ዕዳ ክምችት ላይ የወያኔ አገዛዝ ከመጠንቀቅ ይልቅ በልማት ስም እየተበደረ እያመጣ ባለስልጣናቶቹ ክነአማካሪዎቻቸው በሙስና ተዘፍቀው ያለውን የብድር እዳ ክምችት በተመለከተ ሲጠየቁ አያሳስብም ማለት ጀምረዋል::የዓለም የገንዘብ ድርጅት በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ የብድር ዕዳ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አንፃር ሃምሳ ከመቶ በመድረሱ ጥንቃቄ እንዲደረግ እያሻቀበ የመጣው የዋጋ ግሽበትም ትኩረት እንዲሰጠው ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ እውን የብድር እዳ ክምችት አያሳስብም? ምናልባት ለወያኔዎች አያሳስብም ይሆናል አስፈላጊውን ገንዘብ ሰብስበው ከዘረፉ በኋላ ሾልከው ለማምለጥ ስለሆነ እቅዳቸው በልማት ስም ቴሸፍኖ ሃገር እና ሕዝብን ማሽመድመድ ስለሆነ ራእያቸው ለነሱ አያሳስብም ለለውጥ ሃይሎች ግን አሳሳቢ ጉዳይ ነው ለመጪው ትውልድ ከአሁኑ የባሰ ድህነትን ማውረስ ለማይፈልገው ለአሁኑ ትውልድ አሳሳቢ ስለሆነ ሊተኮርበት ይገባል::የወያኔ ባለስልጣናት እና አማካሪዎቻቸው አያሳስበንም በሚል ትእቢት ተወጥረው ሃገራችንን እየገደሉ ይገኛሉ::

ያለማ ያልተደረገ ያልተሰራ አጋኖ በማቅረብ በፕሮፓጋንዳ አጅቦ በሃሰት በማዜም ወደር ያልተገኘለት ወያኔ ዛሬም ላም ባልወለበት …እንደሚባለው በምርታማ መስኮች ላይ እያዋልነው ነው ብድሩን የሚል የሃሰት ሰበብ እየፈጠረ ሕዝብን ማሳመን ይፈልጋል::የወያኔ አገዛዝ የግሉን ዘርፍ እያቀጨጨ በሙስና ተሳስሮ የፓርቲውን የንግድ ድርጅቶችን እና በዘመድ አዝማድ ልከክልህ እከክልኝ የተሰሩ ቢዝነሶችን እያጧጧፈ በፕሮፓጋንዳው መስክ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ እየሰራሁ ነው በማለት ሊደልል ይሞክራል::የወያኔ አገዛዝ የግሉ ዘርፍ ውስጥ እጁን ከቶ ስራዎችን በእኩይ ተግባሩ እያመሰ እንዴት የግሉ ዘርፍ ያድጋል?የግሉ ዘርፍ የወያኔ እጆች ባይገቡበት ባለሃብቱ በራሱ ሊያሳድጋቸው እና ሊያዳብራቸው ይችላል::ሆኖም በሙስና እርስ በእርስ የሚታከከው አገዛዝ የተበደረው ገንዘብ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ መሸከም ከሚችለው በላይ ስለሆነ አደጋው እየሰፋ ይገኛል::

በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባው የወያኔ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከውጪ ይሚመጣውን ብድር የባለስልጣናት ኪስ ለመሙላት ስለሚውል ብቻ ልማት ፕሮፓጋንዳ ከመሆኑም ባሻገር በተግባር ታዩ የሚባሉት ያልተጠኑ እና እድሜ የሌላቸው ለሃገር የማይጠቅሙ ስራዎች መሆናቸውን በአይናችን ተመልክተናል::አሁንም መፍትሄ ሊሆን የሚችለው የሃገሪቱ የፖለቲካ ምሕዳር በማስፋት ዜጎችን ማንገላታት በማቆም ዜጎች በሃገራቸው ሰርተው እንዳይኖሩ እንዲሰደዱ የሚድረገው ጫና በማስቀረት ማንኛውም የግል ባለሃብት የራሱን ስራዎች ሲሰራ እኩይ የአገዛዙ እጆች እንዲወገዱ ..ወዘተ…ይህንን ለማድረግ ደሞ ያለው የወያኔ ጉጅሌ አገዛ ፍቃደኛ ባለመሆኡ በቅድሚያ ሊወገድ ይገባል::#ምንሊክሳልሳዊ