“…ቢርባቹም እንዳታምፁ…!” መቐለ ዩኒቨርስቲ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Amdom Gebreslasie =
ትናት መቐለ ዩኒቨርቲ በድምፂ ወያነ ሬድዮ የሚያስተላልፈው ፕሮግራም ስከታተል ነበር።
በፕሮግራሙ ስለ የኣዲሱ ዓመት የትምህር መጀመር፣ ስለ ጂቲፒ_2 እየተካሄዱ ያሉት ስልጠናዎች (ስብሰባ) በመካሄድ ላይ መሆኑ፣ በስብሰባው መሃል በዩኒቨርስቲው ስላለ ሙስና በተለይ የምግብ መበላሸትና ችግር ተማሪዎቹ ጠንከር ያለ ሃሳብ ማንሳተቸው ይገልፃል።
የፕሮግራሙ ኣዘጋጆች የምግብ መበላሸትና መዘረፍ ኣስመልክተው ሰልጣኝ ተማሪዎች የጠየቁት ጥያቄ ይዘው ወደ ኣሪድ ዋና ግቢ የሚገኘው ዶክተር ከሰተብርሃን ፅሕፈት ቤት ሄደው ኣነጋገሯቸው።
ባለፈው ክረምት በፌስቡክ ገፄ የክረምት ተማሪዎች በምግብ መበላሸት ምክንያት ኣመፅ ኣንስተው፣ የዶክተር ክንደያ ገብረሂወት (የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት) መኪና መስታወት ሰባብረው እንደነበር፣ ፌደራል ፖሊስም ከፍተኛ ድብደባ መፈፀሙ፣ ኣስተባባሪዎቹ ጨምረው 15 ተማሪዎች እንደታሰሩ መፃፌ ይታወሳል።
በክረምቱ ኣመፅ ላይ ዩኒቨርስቲው የወሰደው እርምጃ እስካሁን ምንም ቃል ሳይተነፍስ የቆየ ሲሆን ትናንት ግን ዶክተር ከሰተብርሃን የተማሪዎች ምግብ የሚቆጣጠሩ ሃላፊ የተማሪዎች ጥያቄ መነሻነት ኣመፅ እንደነበረ ሲያምኑ ችግሩ የዩኒቨርስቲ የጨረታ ኣወጣጥ ሂደት የፈጠረው ክፍተት እንደነበር ገልፀዋል።
ዶክተሩ ለተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልእክት “… የተፈጠረው ዓይነት ችግር ይፈጠር ተማሪዎች በወኪሎቻቸው ኣማካኝነት ብቻ ከመጠየቅ በዘለለ ማንኛውም ዓይነት ዓመፅ ማካሄድ ለቅጣት እንደሚዳርጋቸው መገንዘብ ኣለባቸው…” በማለት ኣስጠንቀዋል።
ዶክተር በዚህ ቃለ መጠይቅ
1) በክረምት የተነሳው ኣመፅ ኣምነዋል።
2) ካሁን በሗላ ተመሳሳይ ረሃብ ቢያጋጥም እንኳ ራባቸው ችለው ታጥፈው መተኛት እንጂ የክረምት ተማሪዎች እንዳመፁት ማመፅ ኣይቻልም። ብለዋል።
በኣሁኑ ወቅት ባገራችን 7.5 ሚልዮን ህዝብ የድርቅ ሰለባ ሁነዋል።
እስከ ጥር ደግሞ ወደ 15 ሚልዮን ያሻቅባል።
የኢትዮጵያ መንግስት በተለይ የትግራይ ክልል መስተዳድር ድርቁ ለመደበቅ እየተጣጣሩ ይገኛሉ።
የሰው ሂወትም በረሃብ እያለፈ ነው። እነዚህ ተማሪዎች ይህ የህዝባቸው ችግር እያዩ እንዳላዩ እንዲሆኑ፣ ራሳቸው ቢራቡም የተቃውም ድምፅ እንዳያሰሙ እየተገዘቱ ናቸው።
እኔ ግን ረሃብ ክፉ ነው። እንኳን ራሳቸው ህዝባቸው ሲራብም መቃወም ኣለባቸው እላለው።
በተያያዘም የGTP-2 ስብሰባ ያልተሳተፉ የዩኒቨርስቲ ሰራተኞች የክረምት ደመወዛቸ እንዲቆረጥ ተደርገዋል።
“…ቢርባቹም እንዳታምፁ…” የሚል የጠገቡ ትእዛዝ የሚያከብር ሰው ይኖራልን……?
ነፃነታችን በእጃችን ነው…!
IT IS SO……!
