የሰማይ ላይ ላሞቻችንን ቆጠራ (Inventory) – ዶክተር ታደሰ ብሩ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የሰማይ ላይ ላም ቁጥር አንድ: መልካም አስተዳደር
ስለዚች የሰማይ ላይ ላማችን በየስብሰባው እንሰማለን። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ስለእሷ ተናግረው አይጠግቡም። ይሁን እንጂ ስለዚች ላማችን ወሬዋ ይሰማል እንጂ እግሮቿ የኢትዮጵያን ምድር ረግጠው አያውቅም። ይህች ላም አንድ ቀን እግሯን መሬት ላይ ታሳርፍ ይሆናል የሚለው ተስፋቸው የተሟጠጠባቸው በአንድ ወቅት የፓርላማ አባል የነበሩ ሰው “እንኳን መልካም አስተዳደር መጥፎም አስተዳደር አላገኘንም” ሲሉ አማረሩ። እኚህ ሰው ተሳስተዋል “መልካም አስተዳደር” አለች – ሰማይ ላይ!
የሰማይ ላይ ላም ቁጥር ሁለት: የህግ የበላይነት
ወያኔ፣ “በህግ አምላክ” የሚልን ሰው ተስፋ ለማስቆረጥ ሲል “የህግ የበላይነት” የተባለችው ተወዳጅዋ ላማችንን በሮኬት ተኩሶ ያመጠቃት በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥላዋ እንኳን አይታይም። ዛሬ በኢትዮጵያ በምድር ላይ እስዋን ተክታ እየሰራች ያለችው ከቆዳና ጭድ የተሰራችው አሳሳች አምሳያዋ (ጎፍላ) ነች። ጎፍላዋ ራስዋ ”የሰማይዋ ላም ቁጥር 2 እኔ ነኝ“ እያለች አብዝታ ታወራለች፤ ጎፍላመቷ የማያውቅ ግን የለም።
የሰማይ ላይ ላም ቁጥር ሶስት፡ ፈጣን እድገት
ከምርጫ 97 ወዲህ የመጠቀችው ሶስተኛዋ ላማችን “ፈጣን እድገት” ትሰኛለች። በዚህ ላማችን ማረግ ያላዘነ የለም። “ቁርስ”፣ “ምሳ” እና “እራት” በደረሰባቸው ሃዘን ምክንያት “ቁምሳ” ወይም “ቁራት” ወደሚል አንድ ቃል ተጠቃለዋል። ይህች የሰማይ ላይ ላም ጉደኛ ባህሪ አላት። በምድር ችጋር ሲበዛ እሷ በሰማይ ትፋፋለች። ሰሞኑን እንኳ ድርቅ ገብቶ በምድር 7.5 ሚሊዮን ሕዝብ ሲራብ እሷሰማይ ላይ ሆና ”በ2020ዓም ድህነት 0% ይሆናል“ የሚል መግለጫ ላከች።
የሰማይ ላይ ላም ቁጥር አራት: ታላቁ የሚሊኒየም ግድብ
ይህች ዝርያዋ በውል ያልታወቀ፤ በድንገት ቡልቅ ያለችልን ተዓምራዊ ድንቅ የሰማይ ላይ ላማችን ነች። ስለዚች ላም የተነገሩ ነገሮች እርስ በርሳቸው የሚጣሉ ቢሆንም ላሚቷ ሰማይ ላይ አለች።
የሰማይ ላይ ላም ቁጥር አምስት: ——
የሰማይ ላይ ላም ቁጥር ስድስት: ——
…..
……