ሙሰኛና ሙሰኛ ጀርባቸውን በሚተሻሹበት አገር ልማት ሃሰት ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
እንደሁኔታው ተስተካክሎ ቀዳዳዎችን መጠቀም አስተዋይነት ነው፡፡ መንገዶች ሁሉ በአንድ በኩል ብቻ ነው የሚሄዱት ብሎ ግትር አለመሆን ታላቅነት ነው!ዕውቀት እያነሰ በመጣ ቁጥር ሐሜትና ስለሰው መተቸት እጅግ የሚዘወተር ነገር እየሆነ ይመጣል፡፡ በዚህም ሳቢያ ችግርን በመላ ከመፍታት ይልቅ ከአፍ አፍ ማዛመት ዋና ሥራ እየሆነ ይሄዳል፡፡በነገር በተተበተበ ማህበረሰብ ውስጥ ለብልሆች ስድቦች የጋራ ይደረጋሉ፡፡ ሐሜትንም ከሰው ሰው ይለዋወጡታል፡፡ይሄ የሆነበት ምክንያት ሐሜትን ማዛመት ከመቅለሉም የበለጠ አዝናኝና አስደሳች በመሆኑ ሲሆን፣ መቼም ቢሆን መቼ የሌሎችን ስህተት መለየትና ታርጋ መስጠት የራስን ህፀፅ ከማየት የቀለለ በመሆኑ ነው::ይሉናል ፀሐፍት፡፡
በየጊዜው ስለሚዲያዎች ክፉ ክፉው ይወሳል፡፡ ሚዲያዎች እንደአስፈሪ ጠላቶች መታየታቸው በየትኛውም ሥርዓት የሚከሰት ጉዳይ ነው፡፡ ያለነገር አይደለም፡፡ መረጃዎች ህብረተሰብን ያነቃሉ፡፡ የአስተሳሰብ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ይህ ግን በአዎንታዊም በአሉታዊም ውጤት ሊፈረጅ ይችላል፡፡ፈላጭ – ቆራጭ መንግሥታት ሁነኛ ጫና በግል ሚዲያዎች ላይ ማሳረፋቸው የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የህዝብ ፍላጐት ብዙውን ጊዜ የሚቀሰቀሰው በድራማዊ ክስተቶችና ስማቸው በገነነ የተከበሩ ሰዎች እንዲሁም ሚዲያውን እንደራሳቸው ቤት ርስተ – ጉልት ባደረጉ ግለሰቦች ነው ይለናል – ዳንኤል ካህኔማን::
የአዕምሮአችንን ውሱንነት መዘንጋት የሚከሰተው እናውቃለን ብለን ባመንበት ነገር ያለን ለከት የለሽ በራስ መተማመን እና የድንቁርናችንን ሙሉ ገጽታ ለመረዳት ብቃት ማጣት እንዲሁም የምንኖርበትን ዓለም በጥርጣሬ መሞላት ልብ አለማለት ነው! በመጨረሻ የአገራችን የኢኮኖሚ ጣጣ ዛሬም መንገድም ኖሮ፣ አበባም ኖሮ፣ ባቡርም ኖሮ፤ ምን ሆነ? የሚለው ነው፡፡ ሙሰኛና ሙሰኛ ጀርባቸውን በሚተሻሹበት አገር ልማት ይኖራል ወይ? የሚለው ጥያቄ መልሱ አንድና አንድ ነው:: ሹም ለሹም ይጐራረሳሉ፤ ድሃ ለድሃ ይላቀሳሉ!!የልማት መርሀ – ግብር ሙስናን አይሽረውም እንደማለት ነው!!