ከሕወሓት መከላከያ ሰራዊት ክ500 በላይ የጦር መኮንኖች የት እንደጠፉ አይታወቅም::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi ከሕወሓት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ውስጥ ከተለያዩ የጦር እዞች እና ክፍሎች 543 የሚሆኑ የጦር መኮንኖች ለየክፍላቸው ሪፖርት ሳያደርጉ በዛው መጥፋታቸው እና የት እንደገቡ እንደማይታወቅ የመከላከያ ሚኒስቴር ሪፖርታዥ ጠቁሟል::ከተለያዩ የጦሩ ክፍሎች የተሰበሰቡ መረጃዎችን አጣቅሶ የቀረበው ሪፖርታዥ እንደሚያመለክተው በሕመም በእረፍት እንዲሁም በተለያይ ስራ ትእዛዝ ክፍሎቻቸውን ለቀው ከሄዱ በኋላ ያልተመለሱ የጦር መኮንኖች የት እንደገቡ እንደማይታወቅ ጠቅሶ ምናልባት ድንበር አቋርጠው ሰራዊቱን ከድተው በጎረቤት አገሮች ዘልቀዋል ሲል ሪፖርታዡ ግምቱን አስቀምቷል::

ወደ ደቡብ ሱዳን ኬንያ እና ኤርትራ አሊያም በተጭበረበረ ሰነደ ወደ ሌሎች ሃገሮች ተጉዘዋል ያለው መረጃው ከቤተሰቦቻቸው ምንም አይነት የመረጃ ፍንጭ አለመገኘቱን አትቷል ሲሉ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተናግረዋል::ምንጮቹ አያይዘው በየእስር ቤቱ በአስተሳሰባቸው እና ጥያቄ በማንሳታቸው የተጋዙ ሞኮኖችን እንደማይጨምር ገልጸዋል::አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ባሉ የማጎሪያ ካምፖች ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ መኮንኖች ካለክስ እና ፍርድ ታስረው እንደሚገኙ ጠቁመዋል::

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የለውጥ ሃይሎች ሚና እና እንቅስቃሴ አለመኖር የሰራዊቱን አባላት እግር ተወርች እንዳሰራቸው እና የለውጥ ሃይሎች በስፋት ተልቀው ወደ ሰራዊቱ መዝለቅ አለመቻላቸው የሰራዊቱ ንቃተ ህሊና እና ወኔ በወያኔ ተጨፍልቆ ስለሚገኝ የለውጥ ሃይሎች አስፈላጊው ስትራቴጂ በመንደፍ የሰራዊቱን ንቃተ ሕሊና በማዳበር ወኔውን አነሳስተው ከጎናቸው ማሰለፍ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል::