በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ስልጠና የተቀመጡ ተማሪዎችን እና መምህራንን በወታደሮች እየተሸማቀቁ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከተለየያዩ የትምህርት ተቋማት አከባቢ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በየአምስት አመቱ ከታሸገበት እየተፈታ ለውይይት የሚቀርበው የማጭበርበሪያ ሽባው የእድገት እና የትራንስፎርሜችን እቅድ ስልተና እና ውይይት ተብለው የተጠሩ የየተቋማቱ ተማሪዎች መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በውይይቱ ወቅት ንቁ ተሳትፎ እንዳናደርግ በወታደሮች እና ፈጥኖ ደራሾች እየተሸማቀቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል::የዩንቨርስቲ ግቢዎች የጦር ካምፕ እስኪመስሉ ድረስ ወታደሮች አፍሠው እያሸበሩን ነው ሲሉ የወያኔ ባለስልጣናትን ወቅሰዋል::
ስልጠና ተብለው በየአደራሹ የከተቱ ተማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ካሁ ቀደምም ይህ ሰነድ ለውይይት ቀርቦ ሕዝቡ ቢወያይበትም ለማዘናጊያ እና ጊዜ ለመግዣ ለማጭበርበሪያ ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚያመጣው ነገር አሊያም የሚሰማልን ሃሳብ የለም ሲሉ ገልጸው ወያኔ በሃገሪቱ እየፈጠረ ያለው ስራ አጥነት ማህበራዊ ዝቅጠት እና የኑር ውድነት የፖለቲካው አስተዳደር ውጤት ስለሆነ የፖለቲካው አስተዳደር ሙሉ በሙሉ ሊለውጥ ይገባል ሲሉ ተማሪዎቹ እና መምህራኑ ተናግረዋል::
ወያኔ እንደለመደው ሕዝብን ለማጭበርበር ስልጠና በማለት የተሽመደመደውን እና ላለፉት አስርት አመታት ያልተሳካውን የትራንስፎርሜሽን እድገት እየደጋገመ ማምጣቱ በቂ የሆነ አማካሪዎች እንዳሌሉት ይጠቁማል ሲሉ ተማሪዎቹ ይናገራሉ::ይመልካም አስተዳደር ለውጥ የፍትህ መረጋገጥ እስካሌሉ ድረስ ሃገሪቱ እየሞተች እንደምትሄድ የገለጹት መምህራኑ መልካም አስተዳደር እና ፍትህ ከተረጋገጠ ወያኔ ያበቃለታል ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል::ስልተንው የቀጠለ ሲሆን ተማሪው መሟገቱን ወታደሮቹም ማሸማቀቃቸውን ቀጥለዋል::