ዳኞች አዳማ ስልጠና ላይ ናቸው በሚል ሰበብ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ለጥቅምት 5 ለ38ኛ ጊዜ ተቀጠሩ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ፍትሕን ከሚደፈጥጡ የወያኔ ባለስልጣናት የሚሰጠውን ውስኔ ለማንበብ የምን ስልጠና ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ያስከተለው የዞን ዘጠን ጦማርያን የዛሬው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ጉዳይ የካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ስልጠና ላይ ናቸው በሚል ሰበብ ጦማርያኑን ማጉላላት ቀጥሏል::ከታሰሩ 531 ቀናትን ያስቆጠሩት ለ37 ጊዜ በወያኔው የፖለቲካ ፍርድ ቤት የሚጉላሉት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ክሳቸው ፖለቲካዊ መሆኑ ከጅምሩ የሚታወቅ ሲሆን በቂ መረጃ ያልቀረበባቸው በመሆኑ ወያኔ አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተተው ፍትህን በአደባባይ ገድሎ እየቀበራት ይገኛል::

ጉዳዩ ዳኞች አዳማ ስልጠና ላይ ስለሆኑ መዝገቡ ለጥቅምት 5/2008 ዓ·ም ተቀጥሯል። ይህም ለጦማሪያኑ በማረሚያ ቤት ተነግሯቸዋል።ለዳኞች የሚሰጠው ስልጠና ሃገሪቷን ላለፉት አመታቶች ያሽመደመደው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስልጠና ዜጎች በፍትህ ላይ ያላቸውን እምነት ከባለፈው የበለጠ የሞተውን ደግሞ ይገለዋል ተብሎ ይጠበቃል::በኢትዮጵያ የሞተው ፍትህ የዜጎችን ይመኖር ሕልውና ከማደፍረሱ ሌላ ያለው አገዛ አለመረጋጋቱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::የዞን ዘጠኝ ጦማርያም ምንም ማስረጃ ይሁን አጥጋቢ ክስ ሳይቀርብባቸው ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ ብቻ የደነበረው ወያኔ እያንገላታቸው ይገኛል::

Minilik Salsawi's photo.