የወረቀት ብር ግራፊቲ ስራችንን ወጥነት እናላብሰው! ለአንድ ወር ያክል በብር ኖቶች ላይ የትግላችንን ሎጎ ብቻ እናሰፍራለን!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የወረቀት ገንዘብ ግራፊቲ ስራችንን ከጀመርን ሳምንት ሆኖናል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከሕዝባችን በኩል የታየው ሞራል እና ተሳታፊነት አስደስች እና አበረታች መሆኑን ዛሬም ዳግም ማየት ተችሏል፡፡ ይህን መሰል ዘመቻዎች የትግላችንን ድምጽ በማጉላት እና በመንግስት ላይ ጫና በማሳደር በኩል ያላቸው ሚና የጎላ ነው፡፡ ወደፊትም ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን ለስኬታቸው ሁላችንም ርብርቦሽ ልናደርግባቸው ይገባል፡፡

ይህንን ስራችንን የበለጠ አገር አቀፍነቱን ለማስፋት ወጥነት ባለው መልኩ የሚሰራበትን ቅርጽ ማስያዝ የተሻለ መሆኑ ታምኖበታል፡፡ በዚህም መሰረት የዚህኑ ስራ አፈጻጸም በተመለከተ በየጊዜው የሚለቀቁ ተጨማሪ የአሰራር መንገዶች ይኖሩናል፡፡ ሁሉንም ወቅቱ ሲደርስ ይፋ የምናደርግ ይሆናል፡፡ እስከዚያው ግን የገንዘብ ግራፊቲ ስራችንን በሚከተሉት መመሪያዎች መሰረት በማከናወን እና ላልሰሙት ሁሉ በማዳረስ እንረባረብ ዘንድ እንጠይቃለን!

1/ ከዛሬ መስከረም 24/2007 ጀምሮ ለሚቀጥለው አንድ ወር ያክል በወረቅት ብር ላይ የምንፅፈው የትግላችንን አርማ (ቀይ ክብ ቀለበት ውስጥ አንድ ቁጥር ያለበትን) ብቻ ይሆናል፤

2/ አርማችን የተጻፈባቸውን የብር ኖቶች የበለጠ ለማሰራጨት በዚህ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምንሰግድባቸው አራት ጁሙዓዎች ከተጻፈባቸው የ1 ብር ኖቶች ውስጥ አንዱን በየጁሙዓው ሰደቃ እንሰጣለን፤

3/ የምናስቀምጠው አርማ መጠኑ ከምልክትነት ያለፈና ትልቅ መሆን የለበትም፤

4/ አርማውን የምናሳርፍበት ቦታ የገንዘቡ መለያ ቁጥር ላይ መሆን የለበትም፤

ብሄራዊ ጭቆናን አንቀበልም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል! ሰኞ መስከረም 24/2008

አላሁ አክበር!

Minilik Salsawi's photo.