በኢትዮጵያ ከ7.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በከፍተኛ የረሃብ አደጋ እየተጎዳ ነው:: ወደ 15 ሚሊዮን ያድጋል ተብሎ ተፈርቷል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi ካለፈው ነሃሴ ወር 2007 ጀምሮ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በትግራይ አፋር አማራ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል በከፍተኛ ደረጃ በተከሰተው ድርቅ ቀደም ሲል ቁጥሩ ከተጠቀሰው 2.5 ሚሊዮን በረሃብ የተጎዳ ሕዝብ ቁጥሩ አድጎ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የነበረ ሲሆን አሁንም የወያኔው መንግስት የሕዝብን ሃብት አንቆ ወገኖቻችንን ለመርዳት ዝግጁ ባለመሆኑና የለጋሽ አገሮች እርዳታ ለማግኘት የተለመነው ባለመሳካቱ በረሃብ የተጎዳው ሕዝብ ቁጥሩ እየጨመረ ሲገኝ ባሁን ወቅት ሰባት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ በከፍተኛ የረሃብ እደጋ እየተጎዳ መሆኑ ታውቋል::
ይህ የዝናብ እጥረት እና የኤልኒኞ የአየር ጸባይ የፈጠረው ድርቅ ያስከተለው ከፍተኛ የረሃብ አደጋ በመስፋፋት ላይ ቢሆንም በተለያየ ጊዜ የወያኔ ባለስልጣናት ረሃቡን ለመሸፋፈን እና ለመደበቅ ለማደናበር ቢሞክሩም ረሃቡ አግጥጦ በመውጣት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የምግብ እህር ዕርዳታ እደሚያስፈልጋቸው የእርዳታ ድርጅት ባለስልጣኖች እየተናገሩ ይገኛሉ::የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በነሃሴ መጨረሻ ላይ ባወጣው ዘገባ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ሲል ባለፈው አንድ ወር ግን ድርጅቱ ካወጣው ዘገባ በእጥፉ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ውስጥ እየዋኘ እንደሚገኝ ተገልጿል::በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ከ15 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ይጎዳል ተብሎ ሲጠበቅ ይህ ደግሞ በሶሪያ በጦርነት ከሚጎዳው ሕዝብ በላይ መሆኑን ዘገባዎች ይጠቁማሉ::ለዚሁም የተባበሩት መንግስታት አንድ ተግባራዊ እርምጃ ካልተወሰደ አደጋው የከፋ እንደሚሆን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል:: #ምንሊክሳልሳዊ
