የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን … መሬት.. ካሳ.. ነጠቃ.. ጎዳና … አደጋ ….. ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሃገር ቢያድግ ከተሞች ቢስፋፉ ማንም የሚጠላ የለም::በልማት ስም የሚደረጉ ድምጽ አልባ ሽብሮች ግን ለዜጎች ሕልውና አደጋ ስለሆኑ ሊተኮርባቸው ይገባል::መሬት ከመንግስት ባለቤትነት ይልቅ ወደ ግል ይዞታ ቢዞር ለዜጎች የመኖር ሕልውና ጥሩ ነው ከሚሉት ወገን ስሆን መንግስት መሬትን በባለቤትነት ያዘ ማለት ደሞ ዜጎችን የመኖር ሕልውና ከማሳጣቱም በላይ እጅግ አደገኛ መሆኑን ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እያየነው ነው:: የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በተመለከተ በአሁን ሰአት ከሚንጫጩት ውስጥ ትላንትና መሬት የመንግስት ካልሆነ ሞተን እንገኛለን በግል ይዞታ ስር መሬት ከሆነ እነ’እንትና’መሬቱን በገንዘባቸው ገዝተው ይስፋፉና ለኛ አደጋ ነው ሲሉ የነበሩ አጫፋሪዎቻቸው መሬት የገበሬው ቢሆን ገበሬው ባልተመጠነ ካሳ ጎዳና አይደፋም ነበር ሲሉ እያደመጥን ነው::አስቀድሞ ነበር መደቆስ …ትላንት በዘረኝነት በጥላቻ የተባበሩበት ጉዳይ ዛሬ ራሳቸውን ነጥሎ እያጠቃ ነው::
ይህ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የሚሰሙ የደሃው ገበሬ ሮሮ የአምራቹ ሃይል የሕልውና ጉዳይ እናጂ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም::ሌሎች ማስተር ፕላኑን እንቃወማለን ብልው የሚንጫጩት ደግሞ ወያኔን ስለሚጠሉ ብቻ በፖለቲካ ጥላቻ በደፈናው የሚንጫጩ አንድም ብስለቱ ይሁን የጉዳዩ እውቀት የሌላቸው እነፖለቲካ ሱሪያችን እናጥልቅ በአንገታችን የሚባሉ የፖለቲካ ፍጆታ መስሏቸው ነው::ሁለቱም ተቃዋሚ እና የሚሉ ይቅርና አፈናቃዩ ወያኔ ለገበሬው የሚጠቅም ዘላቂ መፍትሄ መሻትን አልታያቸውም እዚህ ጫጫት ሲበዛ መሰሪው ወያኔ ገበሬውን በርካሽ ካስ ጎዳና ላይ ከጣለው በኋላ አራሹን ሃይል አንድም ለቀን ሰራተኝነት አሊያም ለሃብታም ጠባቂነት ይዳርገዋል::በተነጠቀ መሬት ላይ ደሞ ባለሃብት ተብለው የሚመደቡት የአገዛዙ አካላት/ብልቶች ስለሆኑ እናገራለሁ ቢባል ጣጣው ብዙ ስለሚሆን የመተባበር መንፈሱም ስለሚከፋፈል ቤተሰብን የበተነው አምራች ሃይል እግሩ ወዳመራው ይነጉዳል::ይህ እና ቀጣይ መንግስታዊ ሽብሮች የመኖር ሕልውና ያሳጣሉ:;
አዲስ አበባ እንደ ሌሎች አለም አቀፍ ከተሞች እጅግ ሰፊ ብትሆን ማናችንም አንጠላም::የከተሞች እድገት አስፈላጊ ቢሆንም በዘላቂነት ለዜጎች መፍትሄ መስጠት ይገባል::ለገበሬው የገንዘብ እና የምናምንቴ ካሳ ከመስጠት በርካታ ለም መሬቶች ያሌት ኢትዮጵያችን አንዱን ክፍል መሬቱን ለሚነጠቀው ገበሬ ብናሰፍርበት ጉዳቱ ምንድነው:: ከካሳ ይልቅ በምትኩ መሬቱት ሰጥቶ ማቋቋም አምራች ሃይሉን ለማዳበር ይረዳል::ይህን ግን ወያኔ አልፈጠረባትም::የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በተያያዘ በወያኔ ጉልበተኝነት ላለፉት ጊዜያት በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚኖሩ አርሶ አደሮች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ ከባድ የሆነ መንግስታዊ ወንጀል ተፈጽሟል::ዜጎች ተገድለዋል::ታስረዋል::ተሰደዋል:: እስካሁንም ያሉበት የማይታወቅ በርካታ ወጣቶች አሉ ከዚሁ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ::ከዜጎች የመኖር ሕልውና ጋር አደጋ አለው እያልኩ ነው::#ምንሊክሳልሳዊ