በማህበራዊ ሚዲያ የሚያራገበው ዘረኝነት ለዲያስፖራው ትልቅ አደጋ አለው:: ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi – አስታራቂ የለም:: አስታዋይም ጎሏል::ዘመኑስ ወርቅ ነበር ልዩነትን የሚያቻችል እና የሚያቀራርም መጥፋቱ ክፉ ችካል ሆነ የጨለማ ሾተላይ…ይህ መርገምት ነው::በማህበራዊ ሚዲያ የሚያራገበው ዘረኝነት ዲያስፖራውን ሃይል አልባ እና ሽባ ለማድረግ የተዘየደ ነገር መሆኑን ስንቶቻችን እናስታውላለን??? በማህበራዊ ሚዲያ የሚራጨው የዲያስፖራውን መንደር በማመስ እየተንከባለለ የሚበክለው የዘረኝነት አባዜ እና የበታችነት ጉድ አገር ቤት ዘልቆ የገባ ውለት ሕዝብ መሃል የተነከረ እልት ሲያራግበው ለከረመው ዲያስፖራው ትልቅ አደጋ ይሆንበታል::በሃገር ውስጥ በቅጥረኞች እና በካድሬዎች ተባባሪነት ዜጎች ከቀያቸው ሲፈናቀሉ የአንድ አከባቢ ህዝብ ለምን በኖሩነት ቀዬ ምን ባጠፉ ሲል የጎሳ ፖለቲካ ወለድ የሆነው ሕወሓት ሰራሹ የጎሳ ፍልስፍና በመከፋፈል ሕዝቦችን በባርነት እና በማፋጀት በበላይነት ለመግዛት የሚደረገው ሩጫ እየገሰገሰሰ ስለሆነ ልንነቃ እና ልንገታው ይገባል::
በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ በፌስቡክ እየተራገበ ያለው የዘረኝነት እሳት ከዲያስፖራው አልፎ አገር እና ሕዝብን በነበልባሉ ይፈጃል::የነገሩ ቆስቋሾች ቅጥረኞች ብቻ ሳይሆኑ ነገር የሚያባብሱ የኦሮሞ ቡድን ይህን አለ የአማራ ቡድን ይህን ተነፈሰ የትግሬው ቡድን ይህን ተናገረ እያሉ ቆስቋሾችን ታግ በማድረግ ነገር የሚያራግቡ አንድም የአስታራቂነት ሚአ የሌላቸው ሲልም የአስታዋይነት ሚና ያልፈጠረባቸው አራግበው አቀጣጥለው እርስ በእርስ ካባሉ በኋላ የላካቸው አካል ስልጣን እንዲለመልም እነሱም በየሰዉ ሃገር የተላኩበት ትምህርት አሊያም ስራ እንዲያድግ አፍራሽ ሚናቸውን ተለሳልሰው እና ተመሳስለው በመርመስመስ እየፈጸሙ ይገኛሉ::ከእንደዚህ አይነት የበግ ለምድ የለበሱ ልዩነትን በማቻቻል እና ሕዝቦችን በማቀራረብ ዙሪያ ስራዎች ሲሰሩ የሚያማቸው ቀበሮዎች ልንጠነቀቅ ይገባል::ሕዝቦችን በጋራ ለማስኬድ እና በመከባበር በመተሳሰብ በመቻቻል አንድነቱን ጠብቆ የኖረን ሕዝብ ለማናከስ እና ሕዝቡ ሲናከስ ስልጣን እና ጥቅም ይዞ በሕዝብ ጫንቃ ለመቀመጥ የሚደረግ ተልካሻ ተግባር ሩቅ መንገድ አያስኬድም :;ዙሪያው ገደል መሆኑንም መዘንጋት ጅልነት ነው::
በዲያስፖራው ዘንድ በስፋት አየተራገበ ያለው ይህ ወያኔ ወለድ በሽታ ዋናው ክስተቱ የገዢው ፓርቲ ሕወሓት የፈጠረበት የበታችነት ስሜት ሲሆን በሕወሓቶች ዘንድ ከበታችነት ለመላቀቅ በሚደረግ መራወጥ የሚፈጠር ጥላቻ ዘረኝነት የሰረጸባቸው ያዩት የሰሙት ሁሉ የሚያስደነብራቸው የበታች መደቦች ኣንድ ጉዳይ በተነሳ ሰኣት ሁሉ ዘር ላይ የሚንጠለጠሉ እና የስልጣን ጥማትን ለማርካት ሲባል የሃገር አና ሕዝብን ሃብት ለመበዝበዝ የነገ ትውልድ ኣደጋ የማይታያቸው ሕዝብን በዘር በመከፋፈል ለመግዛት የሚያደርጉት ደባ ነው። ቆቤ ኦሮሞ ፤ ቤተ ኣማራ ፤ ትግራዋይ ምናምን እየተባለ በወያኔ የደህንነት ተቍማት ስራ የሚደራጁ ክንፎች በነማን እንደሚመሩ በነማን በጀት እንደሚጦዙ የኣጀንዳዎቹ መነሻዎች እነማን እንደሆኑ ምስክር ኣያስፈልግም።ይህ ወያኔ ወለድ የሆነ የዘረኝነት በሽታ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያህል ባይስፋፋም በዲያስፖራው ዘንድ ግን ስር የሰደደ በሽታ ከሆነ ሰነባብዋል።ጥቂት ዲያስፖራዎች በሃገር ቤት ያሉትን ወጣቶች በገንዘብ በመግዛት ዘረኝነትን ለማስፋፍት ሲጣጣሩ ይስተዋላል።ሆኖም ግን በማህበራዊ ሚዲያ የሚያራገበው ዘረኝነት ለዲያስፖራው ትልቅ አደጋ አለው::ሳናውቅ ክዚህ አፍራሽ የዘረኝነት አባዜ የተደባለቅን ካለ በሰከነ አእምሮ ስለ ሕዝቦች አንድነት እና ዘላቂ ፍቅር ማመዛዘን እና በጋራ መቆም ሲገባን ጥርስ የሚያነካክስ የፈጠራ ታሪክ ላይ ተደብቀን ባንዘባርቅ መልካም ነው::ዛሬ ቢመስለንም በማህበራዊ ሚዲያ የሚያራገበው ዘረኝነት ነገ ለዲያስፖራው ትልቅ አደጋ አለው::#ምንሊክሳልሳዊ