የወያኔው መንግስት እና መጅሊስ ሳኡድ አረቢያ ውስጥ በተከሰተው አደጋ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት አልተወጡም:
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ለሃጂ ጸሎት ወደ መካ መዲና ሳኡድ አረቢያ ተጉዘው ሰሞኑን በደረሱ አደጋዎች የሞቱ እና የት እንደገቡ የአልታወቁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን በተመለከተ የወያኔው አገዛዝ የተጓዦችን ስም ዝርዝር ከመለጠፍ እና ሰበብ ከመፍጠር ውጪ ካለበት ሳይንቀሳቀስ ዝምታም መምረጡን በሃገሪቱ ያለው መንግስት ለዜጎች ደህንነት ያለውን አቋም ያሳያል ሲሉ በጉዳዩ የተቆጩ ኢትዮጵያውያን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ::የሌሎች ሃገራት መንግስታት ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ የዜጎቻቸን ደህንነት እና የጠፉትን በማፈላለግ ስራ ላይ ተጠምደው ባሉበት በዚህ ወቅት የወያኔው አገዛዝ አንድ አገር እና ሕዝብ እመራለሁ እያለ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ካለመወጣቱም በላይ ኤምባሲው ስልክ ቁጥር ከመለጠፍ ውጪ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም እንዳልሰራ ታውቋል::
በሳኡድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ እየተረዳዱ የሞቱ በአደጋው የተጎዱ እና የጠፉ ኢትዮጵያውያን በመርዳት ረገድ ትልቅ ስራ እየሰሩ እንደሆነ በማህበራ ድህርገጽ የሚወጡ መረጃዎች ሲያመለክቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚባለው አካል ግን ለሃጅ ጸሎት በሕጋዊ መንገድ የገቡ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ምስላቸው አድራሻቸው ስማቸውና ዝርዝር መረጃቸው በእጁ እያለ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማድረጉ ስም ዝርዝር በመለጠፍ ብቻ መፍትሄ እንደማይሆን እየተገለጸ ይገኛል::እንዲሁም የመጅሊስ ባለስልጣናት ነገሩን ለማድበስበስ ዝም ማለታቸው የበለጠ ጉዳዩን እንደማያውቁት ሃላፊነት አለብን አያሉ ድምጻቸውን ማጥፋታቸው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን አሳዝኗል::
የማህበራዊ ድህረገጾች የነበረውን አደጋ ተከትሎ የት እንደገቡ በአልታወቁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ፎቶዎች ተጥለቅልቀው በአፋልጉኝ ማስታወቂያ ተወጥረው በሰነበቱበት በዚህ ሰአት ላይ የወያኔ መንግስት እና መጅሊስ የሚተበቅባቸውን ሃላፊነት አለመወጣታቸው ሕዝብን አሳዝኗል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::