ዘረኝነት መድሃኒቱ ያልተገኘለት ትልቁ በሽታ እና የበታችነት አባዜ (ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ይህን ሰሞን እያየን ያለነው ጉዳይ አጅግ የሚገርም እና የለውጥ ሃይል ነን የሚሉ ኣማሳኞች ሳይቀሩ አየተራወጡ ያሉበት የዘረኝነት መነባነብ በኣገሪቱ ስር አንዳይሰድ ትውልዱ እንዳይበከል የሚያስፈራ ጉዳይ መሆኑ ውሎ ኣድርዋል፥፥የሚደርሱኝ መረጃዎች አንደሚጠቁሙት ዘረኝነትን ለማስፋፋት የተለያዩ ኣካላት ገንዘብ መድበው በሃገር ቤት ያለውን ወጣት ለፍጅት እና ለኣጀንዳቸው ማስፈጸሚያ አያጩት ነው።ይህ ደግሞ የሕወሓት አጅ የለበትም ማለት ዘበት ነው። ሕወሓት ወንጀለኘ አና ኣሸባሪ ዘረኛ እና ኣስመሳይ ማፊያ እና ዘራፊ ሕገወጥ ድርጅት ነው።

በዲያስፖራው ዘንድ በስፋት አየተራገበ ያለው ይህ ወያኔ ወለድ በሽታ ዋናው ክስተቱ የገዢው ፓርቲ ሕወሓት የፈጠረበት የበታችነት ስሜት ሲሆን በሕወሓቶች ዘንድ ከበታችነት ለመላቀቅ በሚደረግ መራወጥ የሚፈጠር ጥላቻ ዘረኝነት የሰረጸባቸው ያዩት የሰሙት ሁሉ የሚያስደነብራቸው የበታች መደቦች ኣንድ ጉዳይ በተነሳ ሰኣት ሁሉ ዘር ላይ የሚንጠለጠሉ እና የስልጣን ጥማትን ለማርካት ሲባል የሃገር አና ሕዝብን ሃብት ለመበዝበዝ የነገ ትውልድ ኣደጋ የማይታያቸው ሕዝብን በዘር በመከፋፈል ለመግዛት የሚያደርጉት ደባ ነው። ቆቤ ኦሮሞ ፤ ቤተ ኣማራ ፤ ትግራዋይ ምናምን እየተባለ በወያኔ የደህንነት ተቍማት ስራ የሚደራጁ ክንፎች በነማን እንደሚመሩ በነማን በጀት እንደሚጦዙ የኣጀንዳዎቹ መነሻዎች እነማን እንደሆኑ ምስክር ኣያስፈልግም።

ይህ ወያኔ ወለድ የሆነ የዘረኝነት በሽታ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያህል ባይስፋፋም በዲያስፖራው ዘንድ ግን ስር የሰደደ በሽታ ከሆነ ሰነባብዋል።ጥቂት ዲያስፖራዎች በሃገር ቤት ያሉትን ወጣቶች በገንዘብ በመግዛት ዘረኝነትን ለማስፋፍት ሲጣጣሩ ይስተዋላል።ኣለም በኣንድ የእድገት መሰረት ላይ ለመመስረት በቴክኖሎጂ እና ትልልቅ ግኝቶች ላይ ባተኮረበት በዚህ ዘመን ጥቂቶች የሚፈጥሩት የድህረገጽ የዘረኝነት ወከባ አጅግ ኣሳዛኝ እና ኣስደንጋኝ ነው።ሕወሓት አነዚህን በቆሸሸ ታሪክ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሰዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ ኣጀንዳውን ለማስፈጸም አየሮጠ ነው።በዲያስፖራው ጉያ ስር ተወኅቀው የወያኔን የዘረኝነት ኣጀንዳ ለመፈጸው አያወቁም ሳያውቁ ደፋ ቀና የሚሉ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ሊያስቡ ይገባቸዋል።የማያዘልቅ ጸሎት ለቅጽፈት መሆኑን ተረድተው ከዘረኝነት በሽታ ሊላቀቁ ይገባቸዋል። በጥቅም ላይ የተመሰረተ ወጣቱ ያላመነበት የዘረኝነት መስፋፋት ውጤቱ በውኩይ ተግባር ላይ ለተሰማሩ ዘረኞች ኣደጋ ነው። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬