የቴዎድሮስ ተሾመ “ሦስት ማዕዘን” ፊልም በ ሦስት ዘርፎች አሸናፊ በመሆን ታሪክ ሰራ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ትላንት 26/09/2015 ማምሻውን በውቢቷ ፖርት ኤልዛቤት ከተማ በተካሄደው አስራ አንደኛው የ አፍሪካ ፊልም አካዳሚ አዋርድ ላይ፣ በ ስምንት ዘርፎች እጩ ሆኖ የቀረበው የ ቴዎድሮስ ተሾመ “ሦስት ማዕዘን” ፊልም በ ሦስት ዘርፎች አሸናፊ በመሆን ታሪክ ሰራ
Triangle going to America ወይም ሦስት ማዕዘን የመጀመሪያ ሽልማቱን ያገኘው ምርጥ የማጀቢያ ሙዚቃ በሚለው ዘርፍ ሲሆን በዚህም ድምፃዊ ጌትሽ ማሞ ወደ መድረክ በመውጣት የተዘጋጀለትን ሽልማት ተቀብሏል
በዚህ ዘርፍ የናይጄሪያዎቹ ታዋቂ ፊልሞች A place in the star, Iyore እንዲሁም የ አንጎላው Queen of angole እና የሞሪታኒያው Timbectu እጩ ሆነው ቢቀርቡም ሦስት ማዕዘን ፊልምን ያጀበው ጌትሽ ማሞን ሚቆመው አልተገኘም
ቀጥሎ በምርጥ ተዋናይ ዘርፍ በተካሄደ ውድድር አሁንም ሦስት ማዕዘን ፊልም አሸናፊ መሆን ችሏል
በዚህ ዘርፍ የደቡብ አፍሪካው I number number, የናይጄሪያው October, የ ካሜሮኑ Leperdes እና የ ኮትዲቫሩ Run ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት የተወኑ አርቲስቶች ቀርበው በመጨረሻም ኢትዮጵያዊው አክተር ሳምሶን ታደሠ ቤቢ አሸናፊ መሆን ችሏል
ሽልማቱን ለመቀበል ወደ መድረክ የወጣው ሳምሶን ንግግሩን በ አማርኛ ያደረገ ሲሆን በዚህም “…ስለሁሉም የረዳኝን እግዚአብሔር አመሰግናለሁ እዚህ ደረጃ ደርሳለሁ ብዬ በህይወቴ ፈፅሞ አስቤ አላውቅም ነበር አሁን ደስታዬ ወደር የለውም በመጨረሻም ዓለም ወደደም ጠላም አፍሪካ አንድ ትሆናለች” ብሏል
የ አማርኛውን ንግግር ወደ መድረክ በመውጣት ወደ እንግሊዝኛ የተረጎመለት የፊልሙ ደራሲ’ና ፕሮዲውሰር ቴዎድሮስ ተሾመ ነበር
ቀጥሎ በ ሽማግሌዎች ወይም በ እንግዶች ምርጮ የ አፍሪካ ምርጥ ፊልም በሚል ዘርፍ Le president ካሜሩን Timbectu ሞሪታኒያ Oc
tober ናይጄሪያ Run ኮትዲቮር እና I number number ደቡብ አፍሪካ በ እጩ ዘርፍ ቀርበው አሁንም ኢትዮጵያዊው ሦስት ማዕዘን ፊልም አሸናፊ መሆን ችሏልይህን ሽልማት ለመቀበል ደራሲ እና ፕሮዲውሰር ቴዎድሮስ ተሸሞ መሪ ተዋንያኖቹ ሳምሶን ታደሠ ቤቢ እና ሰለሞን ቦጋለ እንዲሁም የ ማጀቢያ ሙዚቃውን የሠራው ድምፃዊ ጌትሽ ማሞ ወደ መድረክ በመውጣት ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ የ ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠን ኢትዮጵያ ሀገሬ የሚለውን ዜማ በጋራ ከተመልካቹ ጋር በማቅረብ ታዳሚውን ማዝናናት ችለዋል።