በአዳማ ከተማ ንፁሃን ሙስሊሞችን የማሰር ዘመቻው ተጠናክሮ ቀጥሏል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው አዳማ ከተማ ማክሰኞ ነሃሴ 26/2007 በተጻፈው የግራፊቲ ፅሁፍ ተከትሎ የከተማዋ ደህንነት ሃይሎች እና የኦሮሚያ ፖሊሶች ሙስሊሞችን እያሰሩ እና እያንገላቱ መሆናቸው ታውቋል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከደህንነት ሃይሎች ጋር በመቀናጀት በአዳማ ከተማ አሰሳውን በማጠናከር ሙስሊሙን እያሸበሩ ሲሆን ይፈለጋሉ በተባሉት ልጆች መኖሪያ ቤት ድንገት በመግባት ልጆቹን ሲያጡ በቤቱ ያገኙትን ሰዎች እያሰሩ እንደነበር ምንጮቻችን የገለፁ ሲሆን እስካሁን 6 ሙስሊሞች መታሰራቸው ተገልፆል።
ከተያዙት ወንድሞቻችን መካከል 5ቱ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከቲታስ ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ የሚገኙ ሲሆን አንዱ ወንድማችን ግን የት እንዳለ ማወቅ አለመቻሉን ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀውልናል።